ደጃፌን ዘግቼ ስልህ አንተ ትሰማኛለህ (2x) በስውር የነገርኩህን በግልጽ ትቀፍለኛለህ (2x) እገባለሁ በሬን እዘጋለሁ ልቤን ደግሞ ላንተ አሳይሃለሁ (2x) ሚረዳኝ የሚረዳኝ ነው (2x) ለኢየሱስ ነገሬን ለሚያውቀው ልግባና የልቤን ላዋየው ሚረዳኝ የሚረዳኝ ነው (2x) ለኢየሱስ ነገሬን ለሚያውቀው የልቤን ነግሬው አልፋለሁ ወደ እልፍኜ ገብቼ በሬን ደግሞ ዘግቼ የልቤን ለአንተ ለአንተ አዋያለሁ ለሰው ባወራው ምን አገኛለሁ የልቤን ለአንተ ለአንተ አዋያለሁ ለሰው ባወራው ምን አገኛለሁ (2x) እገባለሁ በሬን እዘጋለሁ ልቤን ደግሞ ለአንተ አሳይሃለሁ (2x) ትካዜዬን በአንተ ላይ እጥላልሁ የምትደግፍ አንተን ስላየሁ (2x) ለሰው አላወራም ትርፉ መባከን ነው የልብ የሚረዳ ጌታ እንዳንተ ማነው (2x) ከአንተ በላይ ወዳጅ ማን አለ ከአንተ በላይ ረዳት እኮ ማን አለ ከአንተ በላይ ተስፋ ማን አለ ከአንተ በላይ ረዳት እኮ ማን አለ እግዚአብሔር እንዳንተ ማንም የለም (2x) ጌታዬ እንዳንተ ማንም የለም እግዚአብሔር እንዳንተ ማንም የለም ከአንተ በላይ ወዳጅ ማን አለ ከአንተ በላይ ረዳት እኮ ማን አለ ከአንተ በላይ ተስፋ ማን አለ ከአንተ በላይ ረዳት እኮ ማን አለ እግዚአብሔር እንዳንተ ማንም የለም (2x) አምላኬ እንዳንተ ማንም የለም እግዚአብሔር እንዳንተ ማንም የለም