አቤት አምላኬ ያደገልኝን ሳስተውለው ባረኩህ (2x) የእኔ ጌታ ያደረክልኝ ሳስተውሰው ወደድኩህ (2x) ለካስ እንዲህ ነው (3x) ነፍሴን ያዳልቃት ከጉድ ነው ለካስ እንዲህ ነው (3x) ነፍሴን ያዳልቃት ከሞት ነው (2x) የዘለዓለም ፍቅር የዘላለም ሕይወት ይሄው አሰጥቶኛል ወደ አብ መግባት ኢየሱስ አየሁት የፍቅርህን ልኩን አኔ አስገዝቶኛል እስከ ሞት መሆኑ ማንም ባያውቅህ የታወቅህ ነህ ማንም ባያምንህ የታመንህ ነህ እኔስ አውቄህ ሆንኩኝ ምስክር ሳላመነታ ሳልደናገር (2x) እኔስ አውቄ ሆንኩኝ ምስክር ሳላመነታ ሳልጠራጠር ታሪክ ተረድቼ አይደለም ሲነገር ሰምቼ ብቻ አይደለም የሰራህልኝን አስቤ እከተልሃለሁ ከልቤ ታሪክ ተረድቼ አይደለም ሲነገር ሰምቼ ብቻ አይደለም ያደረክልኝን አስቤ እኖርልሃለሁ ከልቤ አውቄያለሁ አውቄያለሁ ተረድቻለሁ የመኖሬ ትርጉም ሆኖ አግኝቼዋለሁ (2x) አቤቱ እንዳንተ ለኔ ማነው ማንስ ነው ልሙትልሽ ያለው ከሰማያት ወርደህ ያዳንከኝ አንተ ለዘለዓለም ልገዛልህ ላንተ ከሰማያት ወርደህ አድነህኛል የሰራህልኝን ልቤ አውቆታል ሳመልክህ በደስታ ሳከብርህ በደስታ ለነፍሴ በሞት ፈንታ መዳን አውጀሃልና (2x) እንግዲህ ነፍሴን ካዳንክልኝማ በደስታ እኖራለሁ በደስታ ላንተ ጌታ በደስታ እኖራለሁ በደስታ እንግዲህ ነፍሴን ካዳንክልኝማ በውዴታ እገዛለሁ በውዴታ ላንተ ጌታ በውዴታ እገዛለሁ በውዴታ