ከተሸሸኩበት መንደሬ መጣ ኢየሱስ ገባ ሰፈሬ ጠራኝ ቀርቦ በቁልምጫው ሊያስገባኝ ወደ ጉያው የወዳጄ የአምላኬ ጥሪው ደርሶኛል ምን አደርጋለሁ ቀሪው ዘመኔን ሰጥቼዋለሁ ይስራበት ይክበርበት ያለው አላማ ፈቃድ ሀሳቡ ይጠቅለል በእኔ ይድረስ ከግቡ ሲጠራኝ (ክብር አይቶልኝ) ሲለየኝ (ክብር አይቶልኝ) ሲቀባኝ (ክብር አይቶልኝ) ሲመርጠኝ (ክብር አይቶልኝ) (2x) መገለጫው ነው መገለጫው ለሰማይ ወኪል የምድር ጨው የምድርን ክፋት መርገም ሰባሪ የሰላም ዘማች ለሰማይ ጥሪ (2x) ሲጠራኝ (ክብር አይቶልኝ) ሲለየኝ (ክብር አይቶልኝ) ሲቀባኝ (ክብር አይቶልኝ) ሲመርጠኝ (ክብር አይቶልኝ (2x) ማያንገራግረው ማያመቻምቸው ትዳር ባለበት ሰፈር ራሱን የማይጠምደው ጠሪውን ሲያስደስተው ሲገኝ በጸና እምነቱ ማረጉ ነው በላዩ ሚታየው ሽልማቱ (2x) ወዶ ዘማች ወዶ ዘማች ለወንጌሉ ወዶ ዘማች ፈቅዶ ዘማች ፈቅዶ ዘማች ለዚህ ጥሪ ፈቅዶ ዘማች ማነው (ወዶ ዘማች) ማነው (ለዚህ ጥሪ) ማነው (ራሱን ሰቶ) ማነው (ጌታውን አስጠሪ) ማነው (እኔ ነኝ) ማነው (እኔ ነኝ) ማነው (እኔ ነኛ) ማነው (ለወንጌሉ) ማነው (ዘማች አርበኛ) ማነው (4x) ማነው