Song Lyrics

ቅድስና

Azeb Melesse
Yenefis Abate
ኧረ እንዴት (3x) ላምልክህ ኧረ እንዴት ልሁንልህ ኧረ እንዴት ላስደስትህ ጌታዬ ኧረ እንዴት ልሁንልህ ብዘምር ባከብርህ ይሄ ያረካሃል ወይስ ብሰብክልህ የቱ ይሻልሃል ልወቀው አምላኬ ምን ያስደስትሃል ልጄ ሆይ አዳምጪ መዘመር መስበኩ ማሸብሸብ መዝለሉ ምን ያደርግልኛል መሰዋት ማብዛቱ የኔ ልብ በደስታ ሃሴት የሚያደርገው በሁለንተናሽን ስትቀደሺ ነው ምታደርጊው ሁሉ በፊቴ ሞገስ የሚያገኘው ዐይኖቼ ሁልጊዜ ሚመለከቱት መንፈሱ ወደተሰበረው ትሁት በቃሌ ወደሚንቀጠቀጥ ሰዉ በሚፈራኝ እደሰታለሁ ታዲያ ይሄ ካስደሰተህ ታዲያ ይሄ ካረካህ ልቀደስልህ ጌታዬ ልቀደስልህ ልቀደስልህ አምላኬ ልቀደስልህ ያለ ቅድስና እግዚአብሔርን ማየት አይቻልምና ሁሌ ልቀደስ ያለ ቅድስና እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልምና ሁሌ ልቀደስ በሕይወቴ አክብሬ አንተን አገልግዬ የዓለምን ምኞት ኀጢአት እምቢ ብዬ በእኔ ደስ እንዲልህ ነውና አላማዬ እኖርልሃለሁ በቅድስናዬ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection