ፍቅር ጌታ ጌታ ፍቅር ኢየሱስ አንተ ብቻ አንተ ብቻ አዝ:- ከወደድኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልውደድህ ካፈቀርኩህ የእውነቴን የእውነቴን ላፍቅርህ ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ የአንተ ፍቅር እንከን የሌለበት አሳልፎ ነፍስን እስከ መስጠት ከዚህ ዕውቀት መማር እንኳን ባልችል እኔ አፍቅሬ አይቻለሁ በምድር አዝ:- ከወደድኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልውደድህ ካፈቀርኩህ የእውነቴን የእውነቴን ላፍቅርህ ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ ሰው ስጥተኀኝ ወድጄ ከልቤ ስገልጥለት ፍቅሬን በስራዬ ሚከፈለውን ዋጋ ከፍያለሁ በሕይወቴ ብዙ አሳልፊያለሁ አዝ:- ከወደድኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልውደድህ ካፈቀርኩህ የእውነቴን የእውነቴን ላፍቅርህ ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ ፍቅር ማለት እራስን መስጠት ነው ለወደዱት ታማኝ መሆን ለአንተ ያለኝን ፍቅር ስፈትሸው ወድሃለሁ ምለው ውሸቴን ነው አዝ:- ከወደድኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልውደድህ ካፈቀርኩህ የእውነቴን የእውነቴን ላፍቅርህ ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ ምላሽ መስጠት ለአንተ ለፍቅርህ ሚሆን ከወደድከኝ ጌታ ላቅርብልህ ምላሽ አንደበቴ በጣም እንደምወድህ ቢመሰክር ውዴ ማሬ ብልህ ምን ይጠቅማል ቃላት ብደረድር ተግባር የለሽ ከሆነ የኔ ፍቅር አዝ:- ከኖርኩልህ የእውነቴን የእውነቴን ልኑርልህ ከመሰልኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልምሰልህ ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ ከአፌ የሚወጣው ክሽን ያለ ያማረ ስራዬ የዓለም ድኖ እንዳልዳነ የእውነት ብወድህ ይሄ ይለውጠኛል ቃሌን ከተግባሬ አንድ አድርግልኝ አዝ:- ከኖርኩልህ የእውነቴን የእውነቴን ልኑርልህ ከመሰልኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልምሰልህ ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ አንተ ትቀጣለህ ሃይለኛ ነህ ብዬ እሳት እንዳልጣል ሲኦልን ፈርቼ ይህን አልፈልግም ባፈቅርህ በቂ ነው ላፈቀሩት መኖር አይከብድም ቀላል ነው አዝ:- ከኖርኩልህ የእውነቴን የእውነቴን ልኑርልህ ከመሰልኩህ የእውነቴን የእውነቴን ልምሰልህ ቃሌ ሌላ ተግባር ሌላ አይሁንብህ የምትወደኝ ጌታ በዘለዓለም ፍቅርህ አንዴ ወደኀኛል በዘለዓለም ፍቅርህ ኢየሱስ ብቻ የልቤ ወዳጅ ነህ የነፍሴ ወዳጅ ነህ