Song Lyrics

ንቃ

Azeb Melesse
Yenefis Abate
ያልተማረውን ተመራማሪ የዚ ቤት ጌታ ነው ባለዲግሪ ያሞካሹታል በዘፈናቸው ያቺኑ ሳንቲም እንዲሰጣቸው (ኦ) ሆያ ሆያ ሆዬ ሆ (2x) ይህ ሆያ ሆዬ መልኩን ቀይሮ ትንቢት በሚለው ስም ተሸፍኖ እውነት በሚመስል ፍፁም ድራማ ተቀነባብሮ እኛም ቤት ገባ አዝ:- ንቃ ክርስቲያን ንቃ በሐሰት ነቢያት አትዘናጋ (2x) ሰው እንደልቡ ዝሙትን ሰርቶ በእርኩሰትና በአመጽ ተሞልቶ ብለው ይሉታን አንተ ጐበዝ እግዚአብሔር መጣ ሊባርክህ (ኦ) ሆያ ሆያ ሆዬ ሆ (2x) ሰርቆ አጭበርብሮ የሚያመጣውን መልካም ነው ብሎ ቢሰጥ ገንዘቡን የበለጠውን ደግሞ እንዲያመጣ አበዛዋለሁ ይልሃል ጌታ (ኦ) ሆያ ሆያ ሆዬ ሆ (2x) ትክክለኛ ነቢዮች አሉ የጌታን ብቻ የሚናገሩ እነርሱንማ መች ሊሰሟቸው ደፍሮ ይሏቸዋል ሟርተኛች ናቸው አዝ:- ንቃ ክርስቲያን ንቃ በሐሰት ነቢያት አትዘናጋ (2x) መንፈስ ቅዱስን ቃሉ እንደሚለው ሌባውን ሌባ ጨዋ አይለው አንተ ያልሆንከውን ነህ የሚልህ ሊጠቅም አይደለም ነው ሊገድልህ አዝ:- ንቃ ክርስቲያን ንቃ በሐሰት ነቢያት አትዘናጋ (2x) ትክክለኛ ነቢዮች አሉ የጌታን ብቻ የሚናገሩ እነርሱንማ መች ሊሰሟቸው ደፍሮ ይሏቸዋል ሟርተኛች ናቸው አዝ:- ንቃ ክርስቲያን ንቃ በሐሰት ነቢያት አትዘናጋ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection