Song Lyrics

ከሁኔታ በላይ

Azeb Melesse
Yenefis Abate
አዝ:- ከሁኔታ በላይ ጌታ የበላይ (2x) (ጌታ የበላይ (2x)) ከእኔ ችግር በላይ ጌታ የበላይ (2x) (ጌታ የበላይ (2x)) ብዙ ጥያቄ እንቆቅልሽ እያለኝ ግን እዘምራለሁ ሁሌ ደስተኛ ነኝ ለእኔ የተከፈለው ትልቅ የደም ዋጋ አይመጣጠንም ከሁኔታዬ ጋር አዝ:- እንቆቅልሼ እያለ ችግር መከራ እያለ ግን እዘምራለሁ ድል አለ ግን እዘምራለሁ መልስ አለ (2x) ከሁኔታ በላይ ጌታ የበላይ (2x) (ጌታ የበላይ (2x)) ከእኔ ችግር በላይ ጌታ የበላይ (2x) (ጌታ የበላይ (2x)) በእንግድነት አገር ለጊዜው ምኖረው በምታልፈው ዓለም ትቼው ለምሄደው ቢሞላ ባይሞላ እኔ ምን ቸገረኝ ስሄድ ምገባበት በሰማይ ቤት አለኝ አዝ:- እንቆቅልሼ እያለ ችግር መከራ እያለ ግን እዘምራለሁ ድል አለ ግን እዘምራለሁ መልስ አለ (2x) ከሁኔታ በላይ ጌታ የበላይ (2x) (ጌታ የበላይ (2x)) ከእኔ ችግር በላይ ጌታ የበላይ (2x) (ጌታ የበላይ (2x)) እንዳላጉረመርም አፌን በምሥጋና ሃዘንተኛ እንዳልመስል ፊቴ እያበራ ኢሄ እንዴት ሆነ ለምትጠይቁኝ ሁሉን የሚያስረሳ አባት ስላለኝ አዝ:- እንቆቅልሼ እያለ ችግር መከራ እያለ ግን እዘምራለሁ ድል አለ ግን እዘምራለሁ መልስ አለ (2x) ከሁኔታ በላይ ጌታ የበላይ (2x) (ጌታ የበላይ (2x)) ከእኔ ችግር በላይ ጌታ የበላይ (2x) (ጌታ የበላይ (2x))
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection