Song Lyrics

እመለሳለሁ

Azeb Melesse
Yenefis Abate
አዝ:- ብዙዎች እንደፈለጋቸው አንተንም ሳይፈሩ የሚኖሩ ናቸው ሲላቸው እንደምኞታቸው ቃልህን ይገልጻሉ እራሳቸው ስተው ሌላውን ያስታሉ አሉ ደግሞ ጥቂት አንተን የሚፈሩ ምህረትህን ታምነው በጽድቅ የሚኖሩ ታጋሽ ቸር ሩህሩህ ምህረትህ የበዛ ለእነሱ ደግ ነህ ጨካኝ ከተቆጣ እኔ ከእነዚህ ጋር ፈጥኜ እስማማለሁ ላለፈው በደሌ ንስሃ እገባለሁ ድንገት ሳትጥለኝ ዛሬ እመለሳለሁ እመለሳለሁ ፍሬም ማያፈራ የደረቀ እንጨት ማይጠቅም ዛፍ ተቆርጦ መጣል ነው በማይጠፋው እሳት ልትመጣ ነው ክብርህን ልትገልጥ ቤትህን ልታጠራ ኀጢአት ልትቀጥፍ ጅራፍህን ይዘህ ተነስተሃልና አይሆንም ብሎ ማነው ባለስልጣን የሚከለክልህ እንዴ ከያዝከኝ የትኛው ብርቱ ነው ከእጅህ የሚያስጥለኝ እመለሳለሁ የኔ መጨረሻ የኔ እድል ፈንታዬ እመለሳለሁ እንደ እንጨቱ እንዳይሆን መልሰኝ ጌታዬ መልሰኝ ጌታዬ መልሰኝ አዝ:- ብዙዎች እንደፈለጋቸው አንተንም ሳይፈሩ የሚኖሩ ናቸው ሲላቸው እንደምኞታቸው ቃልህን ይገልጻሉ/ይጠቅሳሉ እራሳቸው ስተው ሌላውን ያስታሉ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection