አዝ:- ተይ ነፍሴ ከመንገድ አትቅሪ ተይ ነፍሴ ምድረ በዳ አትቅሪ (2x) እርስት አለ ተነሽ እሩጪ መኖሪያ አለ ተነሽ እሩጪ ክብር አለ ተነሽ እሩጪ አክሊል አለ ተነሽ እሩጪ ነፍሴ ሆይ እባክሽን ስሚ ልምከርሽ በደምብ አስተውዪ እያቸው በምድር የሚሮጡ ለሚጠፋው አክሊል ሲተጉ እርግጥ ነው ክርስትና ያማል ከኖሩ ዋጋ ያስከፍላል ከታገልሽ ሁሉም ነገር ያልፋል ጠብቂ ኢየሱስ ይመጣል አዝ:- ተይ ነፍሴ ከመንገድ አትቅሪ ተይ ነፍሴ ምድረ በዳ አትቅሪ (2x) እርስት አለ ተነሽ እሩጪ መኖሪያ አለ ተነሽ እሩጪ ክብር አለ ተነሽ እሩጪ አክሊል አለ ተነሽ እሩጪ እረኛ እንደሌለሽ አትሁኚ እንደማንም መንገድ ላይ አትቅሪ ስጋሽን ጉሽም አድርገሽ ይዘሽ ወደ ርስትሽ ግቢ ጨክነሽ ችግሩን መከራውን መቅመስ ግድ ነው ብድረ በዳን ማለፍ በሜዳው በትዕግስት እሩጪ አቃተኝ ብለሽ አታቋርጬ አዝ:- ተይ ነፍሴ ከመንገድ አትቅሪ ተይ ነፍሴ ምድረ በዳ አትቅሪ (2x) እርስት አለ ተነሽ እሩጪ መኖሪያ አለ ተነሽ እሩጪ ክብር አለ ተነሽ እሩጪ አክሊል አለ ተነሽ እሩጪ ዮሴፍን ወንድሞቹ የጠሉት ለአውሬ ጉድጓድ ውስጥ የጣሉት ያ ሁሉ ግፍ የደረሰበት የእግዚአብሔር ሃሳብ ስላለበት እንዲህ ያለው ምስክር እያለሽ ተይ ነፍሴ ለምን ትደክሚያለሽ ፈተና ለጊዜው ያሳዝናል ኋላ ላይ መልካም ፍሬ ያፈራል አዝ:- ተይ ነፍሴ ከመንገድ አትቅሪ ተይ ነፍሴ ምድረ በዳ አትቅሪ (2x) እርስት አለ ተነሽ እሩጪ መኖሪያ አለ ተነሽ እሩጪ ክብር አለ ተነሽ እሩጪ አክሊል አለ ተነሽ እሩጪ እግዚአብሔር የሰጠሽን ተስፋ ሚያስጥሉ ብዙ ናቸውና አንቺ ግን ታላቅ ዋጋ እንዳለሽ አትዘንጊ ምድራዊውን አይተሽ የእምነትሽን ጀማሪ ፈጻሜ ምሳሌሽን ኢየሱስን እዬ ጨርሰሽ የጀመርሺውን ተቀበይ ሽልማትሽን