አዝ:- ዋስ ጠበቃዬ (2x) ካህኔ ኢየሱስ የነፍስ አባቴ (4x) የእርግብ የፍየል ደም ይፍሰስ መሰዊያ ላድርጋቸው እንድዱት የህዝቡ ኀጢአት እንዲሰረይለት ሚቃጠል መስዋዕት ይቅረብለት ይህ ስርአት ቀረ (4x) መስዋዕቴ ኢየሱስ ሆነ መስዋዕቴ የከበረ (2x) አዝ:- ዋስ ጠበቃዬ (2x) ካህኔ ኢየሱስ የነፍስ አባቴ (4x) ኀጢአትን ማስወገድ የማይችሉ መስዋዕት ሁልጊዜ ሲያቅርቡ እርሱ ግን ለአንዴ ፈጽሞ ቀደሰኝ እራሱን አቅርቦ የአዲስ ኪዳን ልጅ ነኝ (4x) የተሻለ ካህን አለኝ የተሻለ ኪዳን አለኝ (2x) አዝ:- ዋስ ጠበቃዬ (2x) ካህኔ ኢየሱስ የነፍስ አባቴ (4x) ቃልኪዳን ከእኔ ጋር አደረገ ህጉንም በልቤ አስቀመጠ በአዲስና በሕያው መንገድ አስገባኝ በስጋው በደም የአዲስ ኪዳን ልጅ ነኝ (4x) የተሻለ ካህን አለኝ የተሻለ ኪዳን አለኝ (2x) አዝ:- ዋስ ጠበቃዬ (2x) ካህኔ ኢየሱስ የነፍስ አባቴ (4x) እግዚአብሔር የራሱን ፍቅር የገለጠበት ስጦታው እንዴት ካለ ሞት እኔን ያዳነበት ተአምር የምለው በሕይወቴ ኢየሱሴ የነፍስ አባቴ ኦ ኢየሱሴ የነፍስ አባቴ (2x) የውስጤን ሁሉ ማሳየው ሚስጥረኛዬ በአብ ቀኝ የሚቆምልኝ ጠበቃዬ ሚረዳኝ ደግሞም ሚረዳኝ ሊቀ ካህኔ ኢየሱሴ የነፍስ አባቴ ኦ ኢየሱሴ የነፍስ አባቴ (6x)