Song Lyrics

ቀደም ቢል ምን አለ

Azeb Melesse
Yenefis Abate
ወይ አለማወቄ መጠንከሩ ልቤ የተረኩልኝን ይዤ አለቅ ማለቴ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በቃሉ እንደተንተራስኩት ዘመን ተቆጠሩ ፀሐይ ስትጠልቅ ጥላው ሲሸሽም ማታ ጉብዝናው ካለፈ ቢደርስልኝ ጌታ አዝ:- ባለኝ ይሄ መልካም ነገር ቀደም ቢል ምን አለ (4x) ጥርስ ከነቀልኩበት ከአደኩበት ቤቴ አልለይም እያልኩ ከእናት ከአባቴ ይማህተም ለውጥ የማደርግ መስሎኝ ለካ የመንግሥት ነው ይሄ መቼ ገብቶኝ ወደ እግዚአብሔር ግዛት ፈቅጄ ብገባ ሰብሮ ቢያላቅቀኝ ከዚያ ከጨለማስ አዝ:- ባለኝ ይሄ መልካም ነገር ቀደም ቢል ምን አለ (4x) መናኛውም ከፊት መልካሙም ከኋላ እንዲሁ በደመነፍስ ነበር የኔ ስራ ከዛ ተረት ተረት ሕይወት ውስጥ አውጥቶ መንገድ ቢያስጀምረኝ ትርጉም ላለው ኑሮ ቃሉ ቢጣፍጠኝ እንደ ማር ወለላ ልቤን ዘልቆ ፍቅሩ ውስጥ ውስጤ ቢገባስ አዝ:- ባለኝ ይሄ መልካም ነገር ቀደም ቢል ምን አለ (4x) በከንቱ ያለፉት እነዚያ ቀኖቼ ሳስበው ይቆጨኛል የዛሬን አይቼ ዓለምን ሳይቀጫት ወይ እርሷ ሳትቀጨው ብላቴና ሆኖ አንተን ላገኘ ሰው ምንም እንደማያቅ ሞኝ ነው ቢሉትም እንደእርሱስ ብልጥ የለም አላስተዋሉትም አዝ:- እውነት ነው በጊዜ የበራለት እርሱ እድለኛ ነው (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection