Song Lyrics

እውነት ነው

Azeb Melesse
Yenefis Abate
አዝ:- ዓለም ከሚሰጣችሁ ደስታ እኔ ምሰጣቹህ ይበልጣል ያልከው እውነት ነው (3x) ዓለም ከሚሰጣችሁ ሰላም እኔ ምሰጣቹህ ይበልጣል ያልከው እውነት ነው (3x) የዓለምን ደስታ እናሳይሽ ቢሉኝ እኔም ተስማምቼ ተነስቼ ሄድኩኝ የሙዚቃው ጩኀት ጭፈራ ዘፈኑ ለዐይን የሚስበው የመብራት ድምቀቱ ቅልጥ ካለው መንደር እግሬ እንደወጣ ብፈልግ አጣሁት የነበረው ደስታ አወይ አወይ የዓለም ደስታ ብልጭ ብሎ ወዲያው የሚጠፋ ቋሚ የሆነ ደስታ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ከእርሱ ብቻ ነው አወይ አወይ የዓለም ደስታ በኖ የሚያልቅ ልክ እንደጤዛ እውነተኛ የውስጥ ሰላሜ እንደ ኢየሱስ ማን አለ ለእኔ አዝ:- ዓለም ከሚሰጣችሁ ደስታ እኔ ምሰጣቹህ ይበልጣል ያልከው እውነት ነው (3x) ዓለም ከሚሰጣችሁ ሰላም እኔ ምሰጣቹህ ይበልጣል ያልከው እውነት ነው (3x) ክቡሩን ሰው አየሁ እራሱን ሲጥል ትንሹ ትልቁ በወይን ጠጅ ሲሰክር እርግጥ ነው ለጊዜው ደስታንም ይሰጣል ማታ ላይ አስቆ ጠዋት ያስለቅሳል እኔ ስላየሁኝ እመሰክራለሁ የደስታው ምንጭ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው ሁሉም ነገር ቢተርፍ ቢበዛ እንደ ልብህ ብትሆን እንደ አሻህ የሰላሙን ንጉሥ አለቃ ካላገኘህ መቼም አትረካ እግዚአብሔር ጋር ፍፁም የሆነ ማይወሰድ ሰላም እያለ አትባክን አትድከም ይብቃህ እርፍ በል አይ ኢየሱስ ጋር አዝ:- ዓለም ከሚሰጣችሁ ደስታ እኔ ምሰጣቹህ ይበልጣል ያልከው እውነት ነው (3x) ዓለም ከሚሰጣችሁ ሰላም እኔ ምሰጣቹህ ይበልጣል ያልከው እውነት ነው (3x) አንዱ ለመደሰት ሲደክም ሲለፋ ሌላው ሰላም አጥቶ እራሱን ሲያጠፋ ዓለም ልትሰጠኝ የማትችለው ሃብቴ ከላይ ያገኘሁት ትልቁ ንብረቴ ምንም ነገር ሳይኖር እኔ ጋር ያለው እርካታ አሜን ያስብለኛል እንኳን ሆንኩ የጌታ ብርና ወርቅ የማይተካው ሚበልጥ ነው እኔ/አንተ ጋር ያለው አቤት እኔ እድለኛ ነኝ/ክርስትያን እድለኛ ነህ የሚያሳርፍ አምላክ ነው ያለኝ (2x) አዝ:- ዓለም ከሚሰጣችሁ ደስታ እኔ ምሰጣቹህ ይበልጣል ያልከው እውነት ነው (3x) ዓለም ከሚሰጣችሁ ሰላም እኔ ምሰጣቹህ ይበልጣል ያልከው እውነት ነው (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection