አዝ:- አንዳንዱ ንዋይ ፈልጐ ይሄዳል አምላኩን ትቶ ለሚያልፈው ለሚጠፋው ይሄ ሰው እንዴት ሞኝ ነው ተራራ ሕይወት ዳገት ነው/መከራ ሕይወት ሰልፍ ነው ለመኖር ሁሌ ትግል ነው ቢሆንም ለተድላ ብዬ አልሄድም አማላኬን ጥዬ (2x) አዝ:- አንዳንዱ ንዋይ ፈልጐ ይሄዳል አምላኩን ትቶ ለሚያልፈው ለሚጠፋው ይሄ ሰው እንዴት ሞኝ ነው ሌሊት ላይ ፀሐይ እንድትወጣ ብፈልግ መች ይሆንና ለሁሉም ስርአት አለው እንስኪነጋ እጠብቃለሁ (2x) አዝ:- አንዳንዱ ንዋይ ፈልጐ ይሄዳል አምላኩን ትቶ ለሚያልፈው ለሚጠፋው ይሄ ሰው እንዴት ሞኝ ነው እግዚአብሔር ለእኔ ያስቀመጠውን ለማንም እንደማይሰጠው ገብቶናል ተረድቻለሁ እርሱን ትቼ የት እሄዳለሁ (2x) አዝ:- አንዳንዱ ንዋይ ፈልጐ ይሄዳል አምላኩን ትቶ ለሚያልፈው ለሚጠፋው ይሄ ሰው እንዴት ሞኝ ነው አልከዳውም ይሄን ሳወራ ሞራልም አይደል ፉከራ ከልቤ እወደዋለው ያለ እርሱ እንዴት እኖራለሁ (2x) አዝ:- አንዳንዱ ንዋይ ፈልጐ ይሄዳል አምላኩን ትቶ ለሚያልፈው ለሚጠፋው ይሄ ሰው እንዴት ሞኝ ነው