የሰማያት ዳርቻ ሰሪ የምድርም ሁሉ ፈጣሪ አንተ አይደለህም ወይ እግዚአብሔር ኤልሻዳይ ኧረ አንተ አይደለህም ወይ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ አላቋርጥ ማንኳኳቴን እስኪከፈትልኝ ደጁ ፀሎቴንም እስኪሰማ እስኪዘረጋላኝ እጁ ዘንበል እስኪል ከዙፋኑ እስኪበዛልኝ ምሕረቱ ዝም አልልም አላቆምም መፈለጌን ማየት ፊቱን እግዚአብሔር በዙፋኑ ያለው ፀሎቴን ይሰማል አውቃልሁ አምላኬ በማደሪያው ያለው ይራራል ይምራል አምናለሁ ( 2x) እስኪለወጥ በምስጋና የለቅሶ የእንባ ጩኸቴ ሙሉ ሆኖ እንኪመጣ እስኪለቀቅ በረከቴ ከአንደበቱ እስኪወጣ የበረከት ንግግር አልነሳም ዞር አልልም ከዙፋኑ ከእግሩ ስር እግዚአብሔር በዙፋኑ ያለው ፀሎቴን ይሰማል አውቃልሁ አምላኬ በማደሪያው ያለው ይራራል ይምራል አምናለሁ ( 2x) የተስፋውን ቃል አስቦ ሊፈጽመው እስኪነሣ የምድሬኔም ኃጢአት በደል ይቅር ብሎ እስኪረሳ ክብሩን ዳግም እስኪመልስ በቅዱሱ ማደሪያው አላቆምም ክርክሬን እስኪነሣ ከስፍራው የሚሰማ የሚመልስ የሚምር ነው የሚራራ ( 2x) በጎነቱ እጅግ ብዙ በሞገሱ የተፈራ ( 2x) ቸር እንደእርሱ ስለሌለ በምድር ቢሆን በሰማይ ( 2x) አንዲቷም ቀን አታልፍብኝ ያምላኬን ፊቱንሳላይ (፬x)