በዙፋኑ ላይ በማደሪያው ላይ በክብርና በግርማው ሳይለዋወጥ ሳይነዋወጥ እንዲሁ እንደጵና ያለው ከነችሎቱ ከነብርታቱ የሚኖረው ኧረ ይሄ ማነው የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ ፡ እግዚአብሔር እርሱ የእኔ አምላክ ነው እግሮቹ በደመናት ላይ ይራመዳሉ ዓይኖቹ በምድር ዙሪያ ሁሉ ያያሉ አይገለጥም በቋንቋ ታላቅነቱ እኔ ክብር እሰጣለው ለጌትነቱ አይገለጥም በቋንቋ ታላቅነቱ እኔ ስግደት አበዛለው ለጌትነቱ ፍጥረት የሚሰማው የሚወደው ገና ሳይነጋ በማለዳው እግዚአብዜር አለ በዙፋኑ የሚለውን ቃል በመሆኑ እኔም ልዘምር ይህንኑ እግዚአብሔር አለ በዙፋኑ እኔም ልዘምር ይህንኑ አምላኬ አለ በዙፋኑ ፪ በክብር ማን እንደርሱ ከብሯል በኃይል ማን እንደርሱ ኃይሏል ፡ በሥልጣን ማን እንደርሱ ተሹሟል በሞገስ ማን እንደርሱ ደምቋል ፡ በዝና ማን እንደርሱ ታውቋል ፡ ኢየሱስ ከሁሉም ይልቃል ፭ ማደሪያው የተለየ ነው ከአማልክት ሁሉ ለዘለዓለም የሚኖር በሙሉ ኃይሉ ባለግርማና ሞገስ የክብር ጌታ ምሥጋና ክብር አምልኮ ይብዛለት ዕልልታ ባለግርማና ሞገስ የክብር ጌታ ምሥጋና ክብር አምልኮ ይብዛለት ዕልልታ በዙፋኑ ላይ በማደሪያው ላይ በክብርና በግርማው ሳይለዋወጥ ሳይነዋወጥ እንዲሁ እንደጵና ያለው ከነችሎቱ ከነብርታቱ የሚኖረው ኧረ ይሄ ማነው የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ ፡ እግዚአብሔር እርሱ የእኔ አምላክ ነው በክብር ማን እንደርሱ ከብሯል በኃይል ማን እንደርሱ ኃይሏል ፡ በሥልጣን ማን እንደርሱ ተሹሟል በሞገስ ማን እንደርሱ ደምቋል ፡ በዝና ማን እንደርሱ ታውቋል ፡ ኢየሱስ ከሁሉም ይልቃል ፭ በዙፋኑ ላይ በማደሪያው ላይ በክብርና በግርማው ሳይለዋወጥ ሳይነዋወጥ እንዲሁ እንደጵና ያለው ከነችሎቱ ከነብርታቱ የሚኖረው ኧረ ይሄ ማነው የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ ፡ እግዚአብሔር እርሱ የእኔ አምላክ ነው