Song Lyrics

አንተን ሳመልክ

Anten Samelk

Azeb Hailu
Special Edition
የኔ ጉልበት ቢንበረከክ፤ ነፍሴን ባፈስ ፊትህ ብወድቅ አንተን አምላኬን ሳመልክ አንተን አንተን ጌታዬን ሳመልክ አንተን እኔ አንተን አምላኬን ሳመልክ አንተን አንተን ጌታዬ ሳመልክ አንተን ክብሬ ይሄ ነው ደስ ታዬ የምወደው ትልቁ ስራዬ ህይወቴም እኮ ነው ኑሮዬ አንተ ማምለክ ውዱን ጌታዬን (፪×) ታማ ነበር ነፍሴ ፤ ታማ ነበር አዎ ከሀጥያት ማጥ ገብታ ፤ ከማትወጣው ከወደቀችበት ጉርጓድ እጁን ሰዶ ያወጣት ጌታ ነው ከሰማያት ወርዶ (፪×) ዛሬም እንዳመሰግንህ ፤ ዛሬም ክበር እንድልህ (፪×) ዛሬም ይጎተጉተኛል (ይቀሰቅሰኛል) ኦሆሆ፤ ዛሬም የበዛው ፍቅርህ ከእግዚአብሔር ቁጣ ከፍርዱ በታች እንድሆን የሚሻ የነፍሴ አሳዳጅ የህይወቴ ቤዛ ስራውን አፍርሶ ጽድቁን አለበሰኝ የኔን መርገም ለብሶ (፪×) ክብሬ ይሄ ነው ደስ ታዬ የምወደው ትልቁ ስራዬ ህይወቴም እኮ ነው ኑሮዬ አንተን ማምለክ ውዱን ጌታዬን (፪×)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection