Song Lyrics

በመጀመሪያ

Azeb Hailu
Bemejemeria Egziabher
የእግዚያብሔር ግርማ ክብርና ሞገሱ በፍጥረት ሁሉ ላይ ታይቶ ያወራል ስለእርሱ ፍቅሩ ርህራሄው ቸርነት ምሕረቱ ሁሉም ይዘምራል በዜማ አንደበቱ ሁሉን ቻይነቱ ሳይሆን ገና ሰማይ ሳይሆን ገና ምድር መጀመሪያ እግዚአብሔር ነበር በላይ እና በታች የሚባል ሳይኖር አስቀድሞ እግዚአብሔር ነበር ሳትታይ ጨረቃ ሳትበራ ፀሐይ እግዚአብሔር አምላክ ቀድሞ አልነበረ ወይ ጥዋት እና ማታ ተብሎም ሳይለይ በሥልጣን በክብር እርሱ አልነበር ወይ አዝ፦ በመጀመሪያ እግዚአብሔር በመጀመሪያ በመጀመሪያ የእኔ አምላክ በመጀመሪያ ከሁሉ በፊት እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ነበር እርሱ መጀመሪያ ሃሌሉያ ( 2x) ለነበረው ላለው ለሚኖረው ሕያው አምላክ ልዑል እግዚአብሔር የሰራችሁ ፍጥረታት በሙሉ በመገዛት አሜን ክበር በሉ ( 2x) የውሃው ክምችት ሳይባል ባሕር መጀመሪያ እግዚአብሔር ነበር ምድርም ሳታበቅ ቡቃያና ሳር አስቀድሞ እግዚአብሔር ነበር ሳይለዩ ገና ውሃና መሬቱ እግዚአብሔር አለ በኃይል በችሎቱ እለታት ዓመታት ዘመናት ሳይሆኑ እርሱ እንዳለ አለ በክብር ዙፋኑ አዝ፦ በመጀመሪያ እግዚአብሔር በመጀመሪያ በመጀመሪያ የእኔ አምላክ በመጀመሪያ ከሁሉ በፊት እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ነበር እርሱ መጀመሪያ ሃሌሉያ ( 2x) ሳይሰራ አዳም ሳትመጣ ሄዋን መጀመሪያ እግዚአብሔር ነበር እፍ ሳይልበት ገና እስትንፋሱን አስቀድሞ እግዚአብሔር ነበር ሳይባሉ ገና ብዙ እና ተባዙ ምድርን አስተዳድሩ ፍጥረታትን ግዙ አዳም ሕያው ሆኖ ሳይመላለስ በማደሪያው አለ የክብር ንጉሥ ስሙም ቅዱስ አዝ፦ በመጀመሪያ እግዚአብሔር በመጀመሪያ በመጀመሪያ የእኔ አምላክ በመጀመሪያ ከሁሉ በፊት እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ነበር እርሱ መጀመሪያ ሃሌሉያ ( 2x) ለነበረው ላለው ለሚኖረው ሕያው አምላክ ልዑል እግዚአብሔር የሰራችሁ ፍጥረታት በሙሉ በመገዛት አሜን ክበር በሉ ( 2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection