Song Lyrics

እድንበታለሁ

Azeb Hailu
Special Edition
ታላቅ የሆነውን ስምህን ጠራዋለሁ በህይወቴ ዘመን እታመነዋለሁ (አመልጥበታለሁ እድንበታለሁ ስምህን እጠራዋለሁ) 2x እግዚአብሔር ስምህ እግዚአብሔር ነው ለዘመናት ሁሉ የተከበረ ከሃይልና ደግሞም ከብርታቱ ያልተገታ ያልተከለከለ ዛሬም ይሰራል ያድናል ጨለማውን ብርሃን ያደርጋል ስምህ በሃይል ይሰራል ዛሬም ይሰራል ያድናል ተራራውን ሜዳ ያዳርጋል ስምህ ሃይል አለው ይሰራል ታላቅ የሆነውን በላይ በታች ካለው ፍጥረት ከሚመጣውም አለም ከሚጠሩት ስሞች መካከል እንዳንተ ያለ የለም ባህር አይታ የሸሸችህ ተራሮችም የዘለሉ አንተን አይተው እንደሆነ መፅሃፍትም መሰከሩ በሰማያት ላይ ታላቅ ነህ በምድርም ላይ አንተ ታላቅ ነህ በፍጥረት ሁሉ ታልቅ ነህ ኢየሱስ አንተ ትልቅ ነህ ጌታዬ አንተ ታላቅ ነው ኢየሱስ ስምህ ታላቅ ነውx2 አንተ እኮ እጅግ ታላቅ ነህ ኢየሱስ ስምህ ታላቅ ነው x2 ወደ አምላኬ ፊት የምቀርብበት የምስጋና ድምፅ የማሰማበት ሞገሴ ነው ስምህ ነው ድፍረቴ መቀበያ መልሽ የለፀሎቴ (የሰማያትን ደጅ ይከፍታል አባት ለልጁ መልስ ይሰጣል ስምህ ሃይል አለው ይሰራል)x2 ታላቅ የሆነውን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection