Song Lyrics

በስምህ ውስጥ

Azeb Hailu
Bemejemeria Egziabher
በስምህ ውስጥ ሃይል አለ በስምህ ውስጥ ሞገስ በስምህ ውስጥ ድል አለ በስምህ ውስጥ ፈውስ የጸና ግምብ ነው ስምህ የጻድቅ መሸሻ ከዚህ ዓለም ግብግብ መሸሸጊያ ዋሻ ከድካም ህመሜ የምፈወስበት ኢየሱስ ያንተ ስም መድሃኒት አለበት ኢየሱስ ኢየሱስ እግዚአብሔር አባት ከፍ ያደረገው ስም አለህ ኢየሱስ ኢየሱስ በምድር በሰማይ ከፍከፍ ያለ ስም አለህ ኢየሱስ ኢየሱስ የዲያብሎስን ቀንበር ሰባሪ ስም አለህ ኢየሱስ ኢየሱስ በጨለማው ላይ ብርሃን አብሪ ስም አለህ ስምህ ማንነትህ ማንነትህ ስምህ እንደተጠራህበት እንደዚያው መሆንህ አዳኝ ሲሉህ አዳኝ ነህ ህይወት ሲሉህ ህይወት ኢየሱስ ያንተ ስም እውነተኛ እውነት ኢየሱስ ኢየሱስ እግዚአብሔር አባት ከፍ ያደረገው ስም አለህ ኢየሱስ ኢየሱስ በምድር በሰማይ ከፍከፍ ያለ ስም አለህ ኢየሱስ ኢየሱስ የዲያብሎስን ቀንበር ሰባሪ ስም አለህ ኢየሱስ ኢየሱስ በጨለማው ላይ ብርሃን አብሪ ስም አለህ በሰልፉ ሜዳ ላይ በውጊያው መንደር ስምህ የጦር እቃችን የማይበገር የልጆችህ አንገት ቀና የሚልበት ኢየሱስ ያንተ ስም ታላቅ ሃይል አለበት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection