Song Lyrics

ላመስግነው

Azeb Hailu
Enitarek
ላሞግሰው ዙፋንህን ላደናንቅ ከእግሮችህ ስር ሆኜ ቅኔን ላፈልቅ አንደበቴን ቀድሼ ዜማ ላፈስ ጌታ ልልህ መጣሁ ክበር ንገሥ እንዲህ ከሚሉ ጋራ ልተባበር እኔም የእራሴን ፈንታ ልጨምርልህ ይሄም ትንሽ ነው ለአንተ አይበዛምና ከናፍርቶቼ ይጥሩህ ብለው ገናና አንተ ገናና አንተ ገናና ነህ አንተ ገናና (2x) በላይ ነህ ከዚህም በላይ ነህ በላይ ነህ ከዚያም በላይ ነህ (2x) ከሰማነው እና ካየነው በላይ ነህ ከዚህም በላይ ነህ ከዘመርነው ከሰበክነው በላይ ነህ ከዚያም በላይ ነህ (2x) የለም (3x) ሌላ ጌታ የለም የለም(3x) ሌላ ንጉሥ የለም የለም (3x) ሌላ አዳኝ የለም የለም (3x) ሌላ ገዢ የለም ሌላ ጌታ የለም ሌላ ንጉሥ የለም ሌላ አዳኝ የለም ሌላ ገዢ የለም (2x) በእውነትና በመንፍስ ስትመለክ ፍጥረት ሁሉ በፊትህ ሲል ዝቅ ዝቅ ቋንቋው ሁሉ ስለአንተ ዝና ሲያወራ ሲባል ከአማልክት ሁሉ ነህ የተፈራህ እንዲህ ከሚሉ ጋራ ልተባበር እኔም የእራሴን ፈንታ ልጨምርልህ ይሄም ትንሽ ነው ለአንተ አይበዛምና ገና ፍጥሮችህ ይጥሩህ ብለው ገናና አንተ ገናና አንተ ገናና ነህ አንተ ገናና (2x) በላይ በሰማይ ላለው በዙፋኑ ለሚገዙለት እልፍ ቅዱሳኑ ለሚባርኩ ስሙን በዝማሬ አምላክ ለሆነው ጥንትም ቢሆን ዛሬ (2x) እኔም አለኝ አምልኮ እኔም አለኝ ምሥጋና እኔም አለኝ ዕልልታ በአመታት መካከል ጸንቶ ለሚኖረው ለጌቶቹ ጌታ (2x) ለጌቶቹ ጌታ ለነገሥታት ንጉሥ ለጌቶቹ ጌታ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection