እንሂድ ሲሉኝ ወደ እግዚአብሔር ቤት ደስ ካለኝ ሓሴት ካደረኩት ስሄድማ ስገባ በፊቱ ሲቀበለኝ በብዙ ምህረቱ ይጨምራል ይበዛል ደስታዬ በመንፈሱ ሲነካኝ ጌታዬ በረከቱን ባዘዘበት ስፍራ ከዚያ ልሆን ከቅዱሳን ጋራ ደግነቱን ባዘዘበት ስፍራ ከዚያ ልሆን ከወገኖች ጋራ አምላኬ ሆይ በቤትህ ሰላም አለ ያዘነውን የሚያጽናና እያባበለ (2x) በዓለም ካለው የተለየ ሰላም ደስታ አግኝቻለሁ ወደ ቤትህ እኔ ስመጣ (2x) ወደ ቤትህ ልገስግስ በመንፈስህ እንድዳሰስ ወደ ፊትህ ልገስግስ በእጆችህ እንድዳሰስ ወደ ክብርህ ልገስግስ በውበትህ እንዲለኝ ደስ ወደ ፀጋህ ልገግስ በመንፈስ እንዲለኝ ደስ ሁል ጊዜ በፊትህ የሚቆሙ ጥበብህን ከአንደበትህ የሚሰሙ (2x) ባሪያዎችህ ኧረ እንደምን የታደሉ በማደሪያህ ደፋ ቀና ሁሌ የሚሉ በቤትህ ደፋ ቀና ሁሉ ሚሉ ወደ ቤትህ ልገስግስ በመንፈስህ እንድዳሰስ ወደ ፊትህ ልገስግስ በእጆችህ እንድዳሰስ ወደ ክብርህ ልገስግስ በውበትህ እንዲለኝ ደስ ወደ ፀጋህ ልገግስ በመንፈስ እንዲለኝ ደስ ልዑል መጠጊያ ጥላ ለዚህ ዓለም ሐሩር ከለላ መኖሪያ ነህ በኧረፍት አምላኬ ሆይ የአንተ ቢት ሰው ሁሉ ይኖራል ታምኖ ሳይሰጋ ምን ይሆናል ብሎ በቤትህ በመቅደስህ ምትሸከም አንተ ነህ እንሂድ ሲሉኝ ወደ እግዚአብሔር ቤት ደስ ካለኝ ሓሴት ካደረኩት ስሄድማ ስገባ በፊቱ ሲቀበለኝ በብዙ ምህረቱ ይጨምራል ይበዛል ደስታዬ በመንፈሱ ሲነካኝ ጌታዬ በረከቱን ባዘዘበት ስፍራ ከዚያ ልሆን ከቅዱሳን ጋራ ደግነቱን ባዘዘበት ስፍራ ከዚያ ልሆን ከወገኖች ጋራ