ህልውናህን ሳጣው ከጐኔ ክብርህን ማየቱ ሲሳነው ዓይኔ ድምፅህ ሲጠፋ ሲርቀኝ ከእኔ ያኔ ነው ጌታ ሆይ መሪር ሀዘኔ ያኔ ነው ኢየሱስ ሆይ መሪር ሀዘኔ ያኔ ነው ጌታ ሆይ መሪር ሀዘኔ ፈራለሁ ዝም ስትለኝ ፈራለሁ ሰጋለሁ ድምፅህ ሲጠፋ ሰጋለሁ ወደ ጉድጓድ የሚወርዱትን መስላለሁ ሆሆ ፈራለሁ ዝም ስትለኝ ፈራለሁ ስትደበቀኝ ሲሰወር ፊትህ ዝግ ሲሆንብኝ ደጅ የምሕረትህ ማን አለኝ ብዬ በማን ልመካ ኃይሌም ጉልበቴ ፊትህ ነው ለካ (2x) አትሰወርብኝ አትደበቀኝ ሰምተህ እንዳልሰማ አትሁንብኝ አትሰወርብኝ አትደበቀኝ አይተህ እንዳላየ አትሁንብኝ (2x) ህልውናህን ሳጣው ከጐኔ ክብርህን ማየቱ ሲሳነው ዓይኔ ድምፅህ ሲጠፋ ሲርቀኝ ከእኔ ያኔ ነው ጌታ ሆይ መሪር ሀዘኔ ያኔ ነው ኢየሱስ ሆይ መሪር ሀዘኔ ያኔ ነው ጌታ ሆይ መሪር ሀዘኔ ፈራለሁ ዝም ስትለኝ ፈራለሁ ሰጋለሁ ድምፅህ ሲጠፋ ሰጋለሁ ወደ ጉድጓድ የሚወርዱትን መስላለሁ ሆሆ ፈራለሁ ዝም ስትለኝ ፈራለሁ