Song Lyrics

ክቡር

Azeb Hailu
Enitarek
ከቶ አልደከመም ጉልበቱ ከቶም አልደነዘም ስለቱ ዛሬም አልፈዘዘም ውበቱ ይገርማል የቃልህ ጽናቱ አሁንም ይሰራል ያው ነው በፍጥረት ሁሉ ላይ ገዢ ነው ሰማያት ቢያልፉም ምድር ቃልህ ለዘለዓለም ክቡር አዝ፦ ክቡር (3x) ቃሉ የእግዚአብሔር ክቡር (3x) ድምጹ የእግዚአብሔር ክቡር (3x) የእርሱ ንግግር ድምጹ ተራራውን ያቀልጣል ጠንካራውን ዝግባ ይቆርጣል ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ ይገልጣል ቃልህ ሰማያትን አጽንቷል ምድርን ደግሞ መስርቷል ሕያውን ግዑዙንም ሰርቷል በዘለዓለም ክብሩ ይኖራል አዝ፦ ክቡር (3x) ቃሉ የእግዚአብሔር ክቡር (3x) ድምጹ የእግዚአብሔር ክቡር (3x) የእርሱ ንግግር ወጀብ ነው ወይ አውሎ ንፋሱ ሰምቶ መልስ ያልሰጠው ለድምጹ ግዑዝ ነው ወይ ሕያው ፍጥረት ሰምተው ማይታዘዙት በሰማያት ያሉ በምድር ይገዛሉ ለእግዚአብሔር በሁሉ ላይ ብርቱ ገናና የእኔ ጌታ ብቻ ነውና ከቶ አልደከመም ጉልበቱ ከቶም አልደነዘም ስለቱ ዛሬም አልፈዘዘም ውበቱ ይገርማል የቃልህ ጽናቱ አሁንም ይሰራል ያው ነው በፍጥረት ሁሉ ላይ ገዢ ነው ሰማያት ቢያልፉም ምድርም ቃልህ ለዘለዓለም ክቡር አዝ፦ ክቡር (3x) ቃሉ የእግዚአብሔር ክቡር (3x) ድምጹ የእግዚአብሔር ክቡር (3x) የእርሱ ንግግር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection