ከሚያመልኩ ጋራ ከሚያነግሱህ ጋራ እኔም ተስማምቼ ላንግስህ ማዳንህን ላውራ ፊትህ ከሚሰግዱ በቅኔ ዝማሬ ከእነርሱ ጋር አሜን ልበል እኔም ተጨምሬ ላንግስህ እኔም ተጨምሬ እኔም ተደምሬ ላምልክህ ኢኸው ለአንተ ክብሬ ከመስዋዕት ይልቅ ምሥጋናን ወደሃል አህህ በእውነት በመንፈስ አምልኮ ከብረሃል እንደዳዊት ጥሎ ማንነት ክብሩን አህህ የሚዘልልህን ወደድከው ያንን አህህ አዝ፦ ይገባሃል (3x) ከዚህ በላይ በሰማይም በምድርም አልተገኘምና አንተን መሳይ (2x) አምላክ በመቅደሱ ኪሩቤል ላይ ሆኖ አህህ በረጅም ዙፋን ላይ ከፍ ብሎ ገኖ አህህ ማደሪያውን ከበው ያሉት መላዕክት አህህ አንዱም ለአንዱ ቅዱስ ቅዱስ ነህ ሲሉት አህህ አዝ፦ ይገባሃል (3x) ከዚህ በላይ በሰማይም በምድርም አልተገኘምና አንተን መሳይ (2x) ከሚያመልኩ ጋራ ከሚያነግሱህ ጋራ እኔም ተስማምቼ ላንግስህ ማዳንህን ላውራ ፊትህ ከሚሰግዱ በቅኔ ዝማሬ ከእነርሱ ጋር አሜን ልበል እኔም ተጨምሬ ላንግስህ እኔም ተጨምሬ እኔም ተደምሬ ላምልክህ ኢኸው ለአንተ ክብሬ ቀን ለቀን ሌሊትም ለሌሊት ሲያወጉ በቋንቋቸው የእርሱን ክብር ሲተርኩ ጨረቃና ፀሐይ እያብረቀረቁ እግዚአብሔር ሰራን ሲሉ እያደነቁ አዝ፦ ይገባሃል (3x) ከዚህ በላይ በሰማይም በምድርም አልተገኘምና አንተን መሳይ (2x)