በየእለቱ በየቀኑ በየማለዳው የማየው የጌታዬን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነው በየእለቱ በየቀኑ በየማለዳው የማየዉ የኢየሱሴን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነው የወደዳቸውን ፈጽሞ እስከመጨረሻው ወደደ ልጆቹን ከበደል ልያጻ በእራሱ ላይ ሞትን ፈረደ ከሞት ይልቅ እጅግ ያየለ የበረታ ፍቅር ይዞት ኢየሱስ እራሱን ከፈለ የእኔ መጥፋት አሳዝኖት እነሆ ሲነጋና ሲመሽ ይህን/የእርሱን ፍቅር አስታውሰዋለሁ ሌለ ምሰጠው የለምና ተመስገን ከፍ በል እለዋለሁ (2x) አዝ፦ በየቀኑ በየእለቱ በየማለዳው የማየው የጌታዬን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነው በየእለቱ በየቀኑ በየማለዳው የማየዉ የኢየሱሴን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነው ፍቅር ምን እንደሆን ታወቀ በስራው በኃይሉ በርትቶ ሰማይን ከምድር አስታረቀ በምህረቱ ጉልበት ጐትቶ የጥሉን ግድግዳ ፈረሰ ሆነ እርቅ ሰላም ደስታ የራቀው በሙሉ ቀረበ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን በጌታ አቤት ይሄ ጌታ ቸርነቱ አደራረጉ አስገርሞኛል በእውቀት በችሎታና ጥበቡ ወደ ፍርዱ ግዛት አፍልሶኛል / አድርሶኛል (2x) እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ኧረ ለምን ለምን ግን ይህንን ብቻ አውቃለሁ እኔ መወደዴን ይህንን ብቻ አውቃለሁ መወደዴን በጉያው እቅፉ አስገብቶ እንደሰወረኝ አውቃለሁ ኢየሱስ ሁልጊዜ እንደሚያስብልኝ (2x) አዝ፦ በየቀኑ በየእለቱ በየማለዳው የማየው የጌታዬን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነው በየእለቱ በየቀኑ በየማለዳው የማየዉ የኢየሱሴን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነው