Song Lyrics

እንታረቅ

Azeb Hailu
Enitarek
አፍቅሮኝ ፍቅርን አስተማረኝ የማረኝ ምህረት አድርጊ ያለኝ በጌታ ለካ ይህም ይቻላል ለአሳዳጅ ምህረት ይደረጋል ገዳዬን በእጅህ ላይ አግኝቶ መመለስ መንገድ አሳይቶ እንዲህ ነው ለካ ፍቅር ማለት ሁሉንም መቀበል በምህረት (2x) ምህረት አግኝቼ ምህረት አሰጣለሁ ይቅር ተብዪ ይቅር እላለሁ (2x) ህግ??? ሳናደርግ በመሃከላችን መስዋዕት ለማቅረብ ምነው ችኮላችን ይቅር መባባሉ ማንንስ ገደለ ተቆጥተን መሸ ዋል አደርም አለ እንታረቅ አሃሃሃ እንታረቅ እንታረቅ አሆሆሆ እንታረቅ (2x) አሁን እንታረቅ እርስ በእርሳችን ሳንሰዋ በፊት መስ ዋዕታችንን በአምላካችን ፊት እስቲ እንተቃቀፍ የሰጠውንም ቃል ከቶ አንተላለፍ እንታረቅ አሃሃሃ እንታረቅ እንታረቅ አሆሆሆ እንታረቅ (2x) ምህረት አግኝቼ ምህረት አሰጣለሁ ይቅር ተብዪ ይቅር እላለሁ (2x) ታናሹን ከታላቁ እኩል በአንድነት ማቀፍ መጠየቅ በዳዩን መጠየቅ ይቅርታ ይሄ ነው ወንጌሉ የጌታ ለአፍቃሪ ፍቅር መስጠትማ ያለ ነው በዓለም ከተማ ጨካኝ ነው የሚሉትን ክፉ ይቻላል በወንጌል/በጌታ ማቀፉ (2x) ምህረት አግኝቼ ምህረት አሰጣለሁ ይቅር ተብዪ ይቅር እላለሁ (2x) እንታረቅ አሃሃሃ እንታረቅ እንታረቅ አሆሆሆ እንታረቅ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection