Song Lyrics

ቃላቶች ሁሉ

Azeb Hailu
Enitarek
አዝ፦ ቃላቶች ሁሉ አነሱብኝ ላመሰግንህ ፈልጌ በማንስ ቋንቋ ላሞግስህ የእኔ ጌታ እንዴት አድርጌ አምላኬ ሆይ አምላክ ነህ ንጉሤ ሆይ ንጉሥ ነህ ከዚህስ??? ሌላ ምን ለበልህ ከዚህስ??? ሌላ ማን ልበልህ (2x) ኧረ አንተ ታላቅ ነህ እጅግ ገናና ቃል የማይገልጸው ውበትህ ዝናህ የምድር ቋንቋ የሰው ቃላት ለእኔ አነሰብኝ ላዜምበት በመላዕክቱ ቋንቋ ልሳን ቅዱስ ቅዱስ ነህ ቅዱስ ለበልህ (2x) እስቲ ልጥራው ስምህን ፍፁም ቅዱስ የሆነውን አንተ በራስህ ቅዱስ በማንነትህ ቅዱስ በስራህ ሁሉ ቅዱስ በአደራረግህ ቅዱስ አንተ ብቻህን ቅዱስ በማንነትህ ቅዱስ በስራህ ሁሉ ቅዱስ በአደራረግህ ቅዱስ ቅዱስ ነህ ቅዱስ (ቅዱስ ነህ ቅዱስ) ቅዱስ ቅዱስ (ቅዱስ ኢየሱስ) (2x) አዝ፦ ቃላቶች ሁሉ አነሱብኝ ላመሰግንህ ፈልጌ በማንስ ቋንቋ ላሞግስህ የእኔ ጌታ እንዴት አድርጌ አምላኬ ሆይ አምላክ ነህ ንጉሤ ሆይ ንጉሥ ነህ ከዚህስ ሌላ ምን ለበልህ ከዚህስ ሌላ ማን ልበልህ (2x) የዙፋንህን ክብር ድምቀት የግዛትህን ወሰን ስፋት የጌትነትህን ስልጣን ብቃት የስምህን ዝና አለቅነት በተመረጠው ቃልና ቅኔ ብዘምር/ብቀኘው እንኳን አልረካም እኔ (2x) እስቲ ልጥራው ስምህን ፍፁም ቅዱስ የሆነውን አንተ በራስህ ቅዱስ በማንነትህ ቅዱስ በስራህ ሁሉ ቅዱስ በአደራረግህ ቅዱስ አንተ ብቻህን ቅዱስ በማንነትህ ቅዱስ በስራህ ሁሉ ቅዱስ በአደራረግህ ቅዱስ ቅዱስ ነህ ቅዱስ (ቅዱስ ነህ ቅዱስ) ቅዱስ ቅዱስ (ቅዱስ ኢየሱስ) (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection