የማይደክም የማያረጅ ግሩም አምላክ ፍፁም ወዳጅ ማይሸነፍ የማይረታ እርሱ ብቻውን ሁሌ ጌታ (2x) በሌሊቱ በአራተኛው ክፍል በሌሊቱ እጅግ በከበደው በሌሊቱ ታንኳዬም ሲጨነቅ በሌሊቱ ማዕበሉ ሲገፋው በሌሊቱ ድንገት ከተፍ አለ በሌሊቱ ተገለጠ ጌታ በሌሊቱ የሚያንገላታኝን በሌሊቱ ሊገስጽ ሊመታ የእኔ ጌታ አሃሃሃሃ የእኔ ተስፋ የእኔ ክብር ኢየሱስ የእኔ አለኝታ (2x) አትፍሪ እኔ ነኝ እያለ የሚያበረታኝን እንደጌታዬ እንደኢየሱስ ከወዴት ላግኝ በለመለመው መስክ ሚመራኝ በእረፍት ውኃ ዘንድ አላገኝም በየትም ስፍራ እኔን የሚወድ ይህ ነው አይባልም ብርታቱ ሊያድን ፈጥኖ ደራሽነቱን ጠበቃዬ ነው በጽድቅ ፍርዱ እውነት ነው እርምጃው መንገዱ ሁሉን ቻይ ክንዱን ዘርግቶ አቁሞኛል ከታች አንስቶ የማዳኑን ብርታት ኃይሉን ዘምራለሁ በሌት በቀን የማይደክም የማያረጅ ግሩም አምላክ ፍፁም ወዳጅ ማይሸነፍ የማይረታ እርሱ ብቻውን ሁሌ ጌታ (2x) ብሏልና እናንተ ደካሞች ኑ ወደ እኔ ከነሸክማቹ ስጡኝና የከበዳችሁን እፎይ በሉ እስቲ ላሳርፋችሁ እንደቃሉ የሚያስጨንቀኝን ስተውለት ስሰጠው ነገሬን የመላውቀው ሰላም ወረደብኝ እፎይ አልኩኝ ረሳሁት ችግሬን የእኔ ጌታ አሃሃሃሃ የእኔ ተስፋ የእኔ ክብር ኢየሱስ የእኔ አለኝታ (2x) አትፍሪ እኔ ነኝ እያለ የሚያበረታኝን እንደጌታዬ እንደኢየሱስ ከወዴት ላግኝ በለመለመው መስክ ሚመራኝ በእረፍት ውኃ ዘንድ አላገኝም በየትም ስፍራ እኔን የሚወድ