Song Lyrics

ልዑል ማደሪያህ

Azeb Hailu
Enitarek
አዝ፦ ልዑል መጠጊያህ ሰፊ ነው ልዑል መደሪያህ ምቹ ነው ልዑል ማረፊያህ ሰላም ነው ያለሥጋት እኖራለሁ (2x) ሊያስፈራሩኝ የሞከሩ ሊያጐሳቁሉኝ የጣሩ አልሆነላቸውም በቃ ልዑል አምላክ አለኝ ለካ ስለገባሁ በመዳፉ ጠላቶቼ እንዲያው ለፉ በእኔና በእነርሱ መኻል ብርቱ ቅጥር ጌታ ሰርቷል (2x) ሃ ሃሌሉያ (3x) ሃሌሉያ ሃ ሃሌሉያ (3x) ሃሌሉያ በላባዎችህ ተሸፍኜ በክንፎችህም ተማምኜ እውነት እንደ ጋሻ ከቦኝ ከአደጋ ሁሉ አስጥሎኝ ሳልደነግጥም ሳልፈራ ይኸው ስኖር ከአንተ ጋራ መኖሪያህ ተመችቶኛል ከዚህ ሌላ ምን ያሻኛል (2x) አዝ፦ ልዑል መጠጊያህ ሰፊ ነው ልዑል መደሪያህ ምቹ ነው ልዑል ማረፊያህ ሰላም ነው ያለሥጋት እኖራለሁ (2x) አንተ መታመኛዬ ነህ መሸሸጊያዬ ነው ስምህ ክፉ ነገር አይቀርበኝም መቅሰፍትም አያገኘኝም በመንገዴ እንዲጠብቁኝ መላእክትህን ታዛለህ እግሬም እንዳይሰናከል በእጆችህ ታነሳኛለህ (2x) ሃ ሃሌሉያ (3x) ሃሌሉያ ሃ ሃሌሉያ (3x) ሃሌሉያ ሃ ሃሌሉያ (3x) ሃሌሉያ ሃ ሃሌሉያ (3x) ሃሌሉያ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection