Song Lyrics

የዳዊት

የዳዊት የአብርሃም ልጅ ያሉት ነብያት ቀድመው የተረኩት በድንግል በማርያም ያደረ የትውልድ ሐረግ ያስቆጠረ ልደቱ በቤተልሔም በንጉሥ በሄሮድስ ዘመን እረኞች በግርግም ያዩት ኢየሱስ የእኔ መድኃኒት የይሁዳ ምድር አንቺ ቤተልሔም ከይሁዳ ግዛቶች ከቶ አታንሺም እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ካንቺ ይወጣል ተብሎ እንደተነገረ ኢየሱስ ተወልዷል መልአኩ ወደ ማርያም ገብቶ የሰላም ድምጹን አሰምቶ አምላኬ ፀጋ የሞላብሽ ማርያም ሆይ በይ ደስ ይበልሽ እነሆ ልጅን ትወልጃለሽ ሥሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ በያዕቆብ ቤት ሁሉ ይነግሳል የእግዚአብሔር ልጅ እርሱም ይባላል ነፍሴ ጌታን ትባርከው መንፈሴም አምላኬን ውርደቴን ተመልክቷል የባሪያይቱን ብርቱ የሆነው እርሱ በእኔ ክብሩን ገልጧል ትዕቢተኛን አዋርዶ ትሁቱን አክብሯል ቃል ነበር ቃልም እግዚአብሔር ይህም ቃል በአብ ዘንድ ነበር በእርሱ ሕይወት ትኖራለች ሕይወትም የሰው ብርሃን ነች ከሆነው አንዳች አለእርሱ አልሆነም ሁሉ ሆነ በርሱ ዓለምን ያጸናበት ቃሉ እነሆ ለሚያምኑበት ሁሉ ቃልም ሥጋ ሆነና ፀጋን እውነት ተሞልቶ በእኛ ዘንድ አደረ ክብሩን አየን ጐልቶ በአባቱ እቅፍ ሆኖ አብን የተረከው ቀድሞም የነበረው ቃል ወልድ ኢየሱስ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection