አዝ፦ እቅፍ ድግፍ እቅፍ በምክሩ ድግፍ እቅፍ ድግፍ እቅፍ በቃሉ ድግፍ አርጐ የሚመራ በዘመናት መሃል እየሰባበረ ቅጥሩን የሚያዘልል ማነው እንደ እግዚአብሔር አሃ ማነው እንደ እግዚአብሔር እህ (2x) የአባትነት ፍቅር ምክሩ ሳይለየኝ ማስተማሩ ልክ እንደ ዓይን ብሌን ተንከባክቧት ሕይወቴን (2x) እንዳልወድቅ እንዳልጠፋ እየሰጠኝ ተስፋ ይኸው አለሁኝ በቤቱ እየዘመርኩ ምህረቱን (2x) አዝ፦ እቅፍ ድግፍ እቅፍ በምክሩ ድግፍ እቅፍ ድግፍ እቅፍ በቃሉ ድግፍ አርጐ የሚመራ በዘመናት መሃል እየሰባበረ ቅጥሩን የሚያዘልል ማነው እንደ እግዚአብሔር አሃ ማነው እንደ እግዚአብሔር እህ (2x) በጉያዎቹ ሸሽጐ ከመከራው ቀን ታድጐ ጠላቶቼ እንደጥላ ቀሩና ወደ ኋላ (2x) ያንን ዘመን በእርሱ አልፌ ከሞቱት መሃል ተርፌ ከክብር ጋር ዛሬን እንዳይ ፈቀደልኝ ከሰማይ (2x) አዝ፦ እቅፍ ድግፍ እቅፍ በምክሩ ድግፍ እቅፍ ድግፍ እቅፍ በቃሉ ድግፍ አርጐ የሚመራ በዘመናት መሃል እየሰባበረ ቅጥሩን የሚያዘልል ማነው እንደ እግዚአብሔር አሃ ማነው እንደ እግዚአብሔር እህ (2x) በሃሩሩ በበረሃ አፍለቅልቆ ከአለት ውኃ የመላእክትን መና ከሰማይ ያወርድና (2x) በእሳት አምድ በደመና ከፊት ፊት ይመራና ወደ ተስፋይቱ ምድር ያደርሰኛል በክብር (2x)