Song Lyrics

ምላስ ሁሉ

አላደርግም ለሌላ ስግደት አንተ ብቻ ነህ አባት (2x) አልችልም ለሌላ መንበርከክ አንተ ብቻ ነህ አምላክ (2x) አላሰማም ለሌላ እልልታ ላንተ ብቻ ነው ይህ ጌታ (2x) እኔ አልሰዋም ለሌላ አምልኮ ለሥምህ ብቻ ነው እኮ (2x) አዝ፦ ምላስ ሁሉ ያንተን ክብር ይናገረው ያውራ (2x) ጉልበት ሁሉ ተንበርክኮ ይደነቅ በስራህ (2x) ባሕር ከፍለህ ሕዝብህን ማሻገርህን የልጆችህን ጠላት በዚያ ማስጠምህን በምድረ በዳው ላይ መናን ማውረድህን ከደረቀው አለት ውሃ ማፍለቅህን (ኦሆ) ታምራትህ (ኦሆ) ድንቅህን ሁሉ (ኦሆ) ይናገረው (ኦሆ) ምላስ ሁሉ (ኦሆ) ታምራትህን (ኦሆ) ድንቅህን ሁሉ (ኦሆ) ይዘምረው (ኦሆ) ምላስ ሁሉ አዝ፦ ምላስ ሁሉ ያንተን ክብር ይናገረው ያውራ (2x) ጉልበት ሁሉ ተንበርክኮ ይደነቅ በስራህ (2x) የማይፈወሰውን ደዌ ማዳንህን የሞተውን ከመቃብር ማንሳትህን ሁለት ዓሣ ለአምስት ሺህ ማጥገብህን በውሃም ላይ መሄድ መጓዝ መቻልህን (ኦሆ) ታምራትህ (ኦሆ) ድንቅህን ሁሉ (ኦሆ) ይናገረው (ኦሆ) ምላስ ሁሉ (ኦሆ) ታምራትህን (ኦሆ) ድንቅህን ሁሉ (ኦሆ) ይዘምረው (ኦሆ) ምላስ ሁሉ አዝ፦ ምላስ ሁሉ ያንተን ክብር ይናገረው ያውራ (2x) ጉልበት ሁሉ ተንበርክኮ ይደነቅ በስራህ (2x) ስለ ሰዎች ሃጥያት ራስህን መስጠትህን በመስቀል ላይ ተቸንክረህ መሞትህን ከሙታንም በኩር ሆነህ መውጣትህን በአባትህ ቀኝ ኦ በክብር መሆንህን (ኦሆ) ታምራትህ (ኦሆ) ድንቅህን ሁሉ (ኦሆ) ይናገረው (ኦሆ) ምላስ ሁሉ (ኦሆ) ታምራትህን (ኦሆ) ድንቅህን ሁሉ (ኦሆ) ይመስክረው (ኦሆ) ምላስ ሁሉ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection