ጽድቅን እንዲያወራ ምላሴ እንድትረካ እንድታርፍ ነፍሴ የዋጀኸኝ አምላኬ መድህኔ ከዚህች ዓለም አበሳ ኩነኔ እንዳይረክስ በከንቱ ከንፈሬ እንዳልጥለው ድንቁን ክብሬ ዘመኔን በእጆችህ ያዝክና አራመድከኝ በሕይወት ጐዳና አዝ፦ ተመስገን ተመስገን ተመስገን ልበልህ ደግሜ ከሃጥያት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ (2x) እንድረዳ ማዳንህን እንዳውቀው ልቦናዬን ወዳንተ የመለስከው እንዳያልፈኝ የሕይወቴ መና ሕሊናዬን ለቃልህ አቀናህ በረከሰው ዓለም የቀደስከኝ በጽድቅ መንገድ ላይ የመራኸኝ ከብዙዎች እኔ ተለይቼ ዘምራለሁ መቅደስህ ገብቼ አዝ፦ ተመስገን ተመስገን ተመስገን ልበልህ ደግሜ ከሃጥያት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ (2x) አልመኝም ከእንግዲህ ወደ ውጪ ረክቻለሁ ጌታ አንተን መርጬ የዓለምን ከንቱነት ኮተቷን ንቄዋለሁ ከነማንነቷ ወስኛለሁ ልኖር አስከብሬህ ላፈራልህ ጣፋጭ መልካም ፍሬ ደስ እንዲልህ ሁሌ በእኔ ጌታ እገዛለሁ ፈቅጄ በደስታ አዝ፦ ተመስገን ተመስገን ተመስገን ልበልህ ደግሜ ከሃጥያት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ (2x)