አዝ፦ መገረም ገብቶበት ቃል እንደጠፋዉ የልቤን ለመግለጽ ቋንቋ እንዳጠረዉ በአሰራርህ ነፍሴ ተደንቃ ኖራለች ምሥጋናው አንሶባት እንባን ታፈሳለች ተባረክ ትልሃለች ተመስገን ትልሃለች ከፍ በል ትልሃለች ነፍሴ እጅግ ወዳሃለች (2x) ከገመትኩትና ካሰብኩት በላይ ማዳንህ ሲገለጥ ከላይ ከሰማይ ሲደራረብብኝ ቸርነት ምህረትህ የምለው ሲጠፋኝ አምላኬ በፊትህ እንባ ቋንቋዬን አይፍሰስ ከእግርህ ሥር ያለኝን ምሥጋና ያውጣው ይናገር ይገባሃልና የነፍሴ ስሜቷ እባክህ ዝም አትበል ተቀበላት ጌታ አዝ፦ መገረም ገብቶበት ቃል እንደጠፋዉ የልቤን ለመግለጽ ቋንቋ እንዳጠረው በአሰራርህ ነፍሴ ተደንቃ ኖራለች ምሥጋናው አንሶባት እንባን ታፈሳለች ተባረክ ትልሃለች ተመስገን ትልሃለች ከፍ በል ትልሃለች ነፍሴ እጅግ ወዳሃለች (2x) እንዲሁ ተመስገን ብዬ የማላልፈው ደግሞም በቋንቋዬ በቃል የማልገልጸው በዘመኔ ሁሉ ከቶ የማልረሳው አምላክ ቸርነትህ ለኔስ ብዙ ነው አቤት አሰራርህ እጅግ ይደንቀኛል መናገር ስጀምር እንባ ይቀድመኛል ለማመስገን ቋንቋ ቃል አጥሮኛልና በእንባዬ ላክብርህ ልውደቅ ልስገድና አዝ፦ መገረም ገብቶበት ቃል እንደጠፋዉ የልቤን ለመግለጽ ቋንቋ እንዳጠረው በአሰራርህ ነፍሴ ተደንቃ ኖራለች ምሥጋናው አንሶባት እንባን ታፈሳለች ተባረክ ትልሃለች ተመስገን ትልሃለች ከፍ በል ትልሃለች ነፍሴ እጅግ ወዳሃለች (2x) እግዚአብሔር አምላኬ ሆንከኝ ደስ ብሎኛል ከዚህ በላይ ባርኮት ከቶ የት ይገኛል አንተን ያገኘሁ ቀን ቤት ኑሮዬ ሞላ ለዘመኔ ሁሉ ተገኘለት መላ ምላሽ ባይሆነኝም ይህ የኔ ምሥጋና ላደርግ የምችለው ይሄንን ነውና ስለዚህ ተባረክ እላለሁ ከነፍሴ የምወድህ ጌታ ኢየሱስ ንጉሤ አዝ፦ መገረም ገብቶበት ቃል እንደጠፋዉ የልቤን ለመግለጽ ቋንቋ እንዳጠረው በአሰራርህ ነፍሴ ተደንቃ ኖራለች ምሥጋናው አንሶባት እንባን ታፈሳለች ተባረክ ትልሃለች ተመስገን ትልሃለች ከፍ በል ትልሃለች ነፍሴ እጅግ ወዳሃለች (2x)