Song Lyrics

እምቢ

የጀግና ልጅ ጀግና ነኝ በመስቀል ጣር ያፈራኝ ከሞት ጋራ ተወራርዶ አሸንፎታል አዋርዶ የአንበሳ ልጅ ነኝ አንበሳ ሥሙን ስመዘው ሳነሳ ማንስ ቀርቦ ሊደፍረኝ የኢየሱስ ልጅ እኔ ነኝ (እምቢ) ሕይወት ይሻለኛል (እምቢ) ሰላም ነፃነት (እምቢ) ክብር እያለልኝ (እምቢ) አልሻም ውርደት (እምቢ) ብርሃን ከፊቴ (እምቢ) ደምቆ እየበራ (እምቢ) አልደናበርም (እምቢ) በጨለማው ስፍራ ሲያምረው ሽንፈት ያ ውርደት መጥቶ ነካካኝ ጥቂት መች ልደነግጥ ልፈራ አለኝ ጉልበት የሚያኮራ ሥሙን ጠራሁ ወነጨፍኩኝ ወጥመዱንም ሰባበርኩኝ መታሰቢያው ፈጥኖ ጠፋ ያዳነኝ ሥም ክብሩ ይስፋ (እምቢ) ዳግም አትገዛኝም (እምቢ) ክጄሃለሁ በቃ (እምቢ) አልጭበረበርም (እምቢ) ሙት መንፈሴ ነቃ (እምቢ) እግሬን አቅንቻለሁ (እምቢ) ላልል ወደ ኋላ (እምቢ) የሰማይ ብርሃን (እምቢ) እኔነቴን ሞላ ልሰግድለት እንዳመልከው ምስሉን ሰርቶ ፊቴ አቆመው ውደቂለት ተንበርከኪ የወርቁን ምስል አምልኪ ባልሰግድለት ባላደርገው በእቶን እሳት መጣል ነው በዚያ መጣልን እመርጣለሁ የእርሱን ምስል ከማመልከው [1] (እምቢ) የሚሰገድለት (እምቢ) እያለኝ አምላክ (እምቢ) ለአሕዛብ አማልክት (እምቢ) አልንበረከክ (እምቢ) ሲያምረው ይቅር እንጂ (እምቢ) የኔ ዜማ እልልታ (እምቢ) እርሱ ለአምላኬ ነው (እምቢ) ለጌቶቹ ጌታ ነይ ወደ እኔ ነይ እያለ በቁልምጫ እያባበለ ሊማርከኝ ብዙ ጣረ ግን አልሆነለት ከሰረ ላዩ መስሎ እንዳበባ ውስጡ እሬት ነው ጨለማ ኋላ ጠልፎ ከሚጥለኝ እምቢ ብያለሁ ይቅርብኝ (እምቢ) የዓለምን ጥሪ (እምቢ) የዓለምን ግብዣ (እምቢ) ከቶ አንገናኝም (እምቢ) እስከመጨረሻ (እምቢ) እግዚአብሔርን መፍራት (እምቢ) ያዋጣኛልና (እምቢ) እጅ አልሰጥም ለዓለም (እምቢ) ሞት አለበትና
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection