በግራና በቀኜ ሆናችሁ ልታጠምዱኝ ያሰፈሰፋችሁ በሉ ስሙኝ እስቲ ልንገራችሁ በእኔ ዘንድ ደግሞ ምን ቀራችሁ አትጠጉኝ አትነካኩኝ ተለያየን እኔ የጌታ ነኝ በዓለም ብኖር አይደለሁ የዓለም መኖሪያዬ ለዘልዓለም በዚህች ምድር ፍጹም አይደለም በዚህች ዓለም ፍጹም አይደለም (2x) አዝ፦ (አሃ) ዓይኖቼን አንስቼ (አሃ) ሳይ ወደ ሰማይ (አሃ) በአብ ቤት ቁጭ ያለው (አሃ) በዙፋኑ ላይ (አሃ) ተስፋውን የሰጠኝ (አሃ) መጥቶ ሊወስደኝ (አሃ) የዘላለም አባት (አሃ) ኢየሱስ አለኝ የአምላክ ምክር የልዑል ትምህርቱ የሰማሁት አዋጅ የመንግሥቱ ውስጤ ገብቶ ሰርፆ ልቦናዬ አጣብቆኛል ከውዱ ጌታዬ ጊዜም የለኝ ዓለም ምሰማሽ እረሳሁሽ አንቺም እኔን እርሺኝ በአምላኬ ዘንድ ተሰራልኝ ቤቴ ሰማያዊ ሆኗል ዜግነቴ (5x) አዝ፦ (አሃ) ዓይኖቼን አንስቼ (አሃ) ሳይ ወደ ሰማይ (አሃ) በአብ ቤት ቁጭ ያለው (አሃ) በዙፋኑ ላይ (አሃ) ተስፋውን የሰጠኝ (አሃ) መጥቶ ሊወስደኝ (አሃ) የዘላለም አባት (አሃ) ኢየሱስ አለኝ በዚህ ምድር ቋሚ ነገር የለም ምስቅልቅል ነው ሲኖር በዚህ ዓለም የከበረ ነገ ይዋረዳል ያለቀሰ በተራው ይስቃል ግራ ገብቶት ሰው ሁሉ ሲሰጋ የማምለጫው መንገዱ ሲዘጋ ጌታዬና አምላኬ ነህ ብዬው የእንግድነት ኑሮ ጀምሬያለሁ አገር አለኝ ቤቴ በሰማይ ነው ተስፋ አለኝ ርስቴ በሰማይ ነው (2x) አዝ፦ (አሃ) ዓይኖቼን አንስቼ (አሃ) ሳይ ወደ ሰማይ (አሃ) በአብ ቤት ቁጭ ያለው (አሃ) በዙፋኑ ላይ (አሃ) ተስፋውን የሰጠኝ (አሃ) መጥቶ ሊወስደኝ (አሃ) የዘላለም አባት (አሃ) ኢየሱስ አለኝ የሰው ዕድሜ መች ከሰባው ያልፋል ቢበረታ ሰማንያ ይሆናል ጥቂት ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት ነው የኛ መኖር ተስፋ እኔ ግን መች በምድር እቀራለሁ በሰማይ ቤት መኖሪያ አግኝቻለሁ ጌታ የግል አዳኜ ሆኖኛል በብርሃኑ ብርሃን ወጥቶልኛል የዘላለም ሕይወት ተሰጥቶኛል የፍርድ ቀን ለምን ያሰጋኛል (2x) አዝ፦ (አሃ) ዓይኖቼን አንስቼ (አሃ) ሳይ ወደ ሰማይ (አሃ) በአብ ቤት ቁጭ ያለው (አሃ) በዙፋኑ ላይ (አሃ) ተስፋውን የሰጠኝ (አሃ) መጥቶ ሊወስደኝ (አሃ) የዘላለም አባት (አሃ) ኢየሱስ አለኝ