እጅጉን ሲራራ በብዙ ሲምር ከቶ ያበቃለትን የሞት ፍርድ ሲሽር ሲስብ ወደራሱ ለክብር መንግስቱ እኔ እርሱን የማውቀው በሰፊ ትዕግስቱ መክሮ ሲመልስ ለክብር ሲያበቃ ውጦ ከሚያስቀር ከረግረጉ ጭቃ ታሪክ ቀይሮ ሥምንም ሲለውጥ ነጥቆም ሲታደግ ካንሸራታቹ ድጥ (2x) አዝ፦ይሄ ነው የኔ ጌታ ይሄ ነው አምላኬ የምለው ይሄ ነው ደግ ቸር ያልኩት እግዚአብሔርን የወደድኩት (2x) የተራበው ሲጠግብ ሲረካ ጠጥቶ ሲድን ከጠላቱ ወደ አምላኬ ሸሽቶ በኖርኩበት ዘመን ይሄንን አውቃለሁ መልካም ቸር እረኛ እንደ እግዚአብሔር ማነው ከጥላው በታች ማረፍ የወደደ በዓለም በረሃ ከስሎ የነደደ ሸክሙ ሲራገፍ እፎይ ሲል ሲቀለው በርሱም ሲታሰብ ባይኔ አይቻለሁ (2x) አዝ፦ይሄ ነው የኔ ጌታ ይሄ ነው አምላኬ የምለው ይሄ ነው ደግ ቸር ያልኩት እግዚአብሔርን የወደድኩት (2x) ክፉኛ ተወግቶ ልቡ ለቆሰለ በኃዘን ተከቦ አበቃልኝ ላለ ወዳጅ ይሆነዋል ጌታ ተጠግቶ ቁስሉን ያክመዋል በዘይት ቀብቶ ቀና ሲያደርገው አንገቱን ላይደፋ የሚጤሰውን ጧፉን ሳያጠፋ አትሞትም በሕይወት ትኖራለህ ሲለው የአምላኬን ፍቅር እኔ አውቀዋለሁ (2x) አዝ፦ይሄ ነው የኔ ጌታ ይሄ ነው አምላኬ የምለው ይሄ ነው ደግ ቸር ያልኩት እግዚአብሔርን የወደድኩት (2x) አለኝ ሊቀ-ካህን በላይ በሰማይ አዝኖ የሚራራ ድካሜን የሚያይ ለበደሌ ስርየት ለሐጥያቴ ይቅርታ ሰጠኝ በምህረቱ ይሄ መልካም ጌታ አባባ የሚል የልጅነት መንፈስ ውስጤ አፈሰሰ ቸሩ ጌታ ኢየሱስ መንፈሱን ታጥቅኩኝ ድኛለሁኝ በቃ ሞትና እርግማን ከእንግዲህ አበቃ አዝ፦ይሄ ነው የኔ ጌታ ይሄ ነው አምላኬ የምለው ይሄ ነው ደግ ቸር ያልኩት እግዚአብሔርን የወደድኩት (4x)