Song Lyrics

ደስ የሚለኝ

አዝ፦ደስ የሚለኝ ያኔ ብቻ ነው ያኔ ስትከብር ስትነግስልኝ ምድህኔ የምረካው ያኔ ብቻ ነው ያኔ ከፍ ስትል ስትገንልኝ መድህኔ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ በምስጋናህ ደስ ይለኛል አንተን ማክበር ማሞጋገስ ያረካኛል (2x) ክበርልኝ የኔ ጌታ ክበርልኝ (3x) ንገሥልኝ የኔ ወዳጅ ንገሥልኝ (3x) ሰው ሁሉ ገብቶት ሲያመሰግንህ አምላኬ አንተ ነህ ጌታዬም ሲልህ ሲዘመር ላንተ ሲሆን እልልታ በሁሉም ስፍራ ስትሆን ጌታ ያኔ ነው የኔ ደስታ ስትነግሥልኝ ጌታ (2x) ያኔ ነው የኔ ደስታ ስትከብርልኝ ጌታ (2x) አዝ፦ደስ የሚለኝ ያኔ ብቻ ነው ያኔ ስትከብር ስትነግስልኝ ምድህኔ የምረካው ያኔ ብቻ ነው ያኔ ከፍ ስትል ስትገንልኝ መድህኔ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ በምስጋናህ ደስ ይለኛል አንተን ማክበር ማሞጋገስ ያረካኛል (2x) ክበርልኝ የኔ ጌታ ክበርልኝ (3x) ንገስልኝ የኔ ወዳጅ ንገሥልኝ (3x) ሰው በፈቃዱ ሳይገደድ ጌታን ሲከተል እርሱን ሲወድ በቤቱም ሲኖር ሲቀር ተማርኮ በፍቅሩ ጉልበት ሳይ ተንበርክኮ ያኔ ነው ደስታዬኮ ሲበዛልህ አምልኮ (4x) አዝ፦ደስ የሚለኝ ያኔ ብቻ ነው ያኔ ስትከብር ስትነግስልኝ ምድህኔ የምረካው ያኔ ብቻ ነው ያኔ ከፍ ስትል ስትገንልኝ መድህኔ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ በምስጋናህ ደስ ይለኛል አንተን ማክበር ማሞጋገስ ያረካኛል (2x) ክበርልኝ የኔ ጌታ ክበርልኝ (3x) ንገስልኝ የኔ ወዳጅ ንገሥልኝ (3x) ፍጥረትም ካንተ ሥር ካንተ በታች ሲሆን ሲገዛ ደግሞም ሲመች በሥልጣንህ ቃል ታዞ ሲመራ የገነነውን ስምህን ሲፈራ ያኔ ነው የኔ ደስታ ስትነግሥልኝ ጌታ (2x) ያኔ ነው የኔ ደስታ ስትከብርልኝ ጌታ (2x) አዝ፦ደስ የሚለኝ ያኔ ብቻ ነው ያኔ ስትከብር ስትነግስልኝ ምድህኔ የምረካው ያኔ ብቻ ነው ያኔ ከፍ ስትል ስትገንልኝ መድህኔ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ በምስጋናህ ደስ ይለኛል አንተን ማክበር ማሞጋገስ ያረካኛል (2x) ክበርልኝ የኔ ጌታ ክበርልኝ (3x) ንገስልኝ የኔ ወዳጅ ንገሥልኝ (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection