ከሰማይ የመጣው የውዴ ውብ ቃል ልጄ ወዳጄ ሆይ አንቺ የኔ ሲል በኮረብታዎች ላይ መጣልኝ ሲዘል ሐዘኔን ሊያስረሳ ነፍሴን ሊያባብል (2x) አዝ፦ የነፍሴ የውስጤ የልቤ የሚገባው ወዳጄ በቃሉ መጥቷል ወደ ደጄ ሲያንኳኳ ከፍቼ የክብርን ንጉሥ አስገባለሁ በአፉ ቃል ነፍሴን አጠግባለሁ ወዳጄ ሆይ ተነሽ ውበቴ ሆይ ነይ ክረምቱም አለፈ ብቅ አትይም ወይ አበቦች በምድር ይኸው ተገለጡ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውን ሰጡ በዓለት ንቃቃት ያለሽ እርግብ ሆይ ጊዜው ደርሷልና ነይ እንተያይ እያለ ሲያጽናናኝ ወዳጄ በቃሉ ነፍሴም ተነቃቃች እግሮቼም ዘለሉ አዝ፦ የነፍሴ የውስጤ የልቤ የሚገባው ወዳጄ በቃሉ መጥቷል ወደ ደጄ ሲያንኳኳ ከፍቼ የክብርን ንጉሥ አስገባለሁ በአፉ ቃል ነፍሴን አጠግባለሁ የሥጋና የደሜን የልቤን ትርታ የመንፈሴን ጩኸት የነፍሴን ሙግቷ ከወንድም አልጦ እኔን ሚጠጋጋ ወዳጅ አለኝና ለርሱ ብቻ ላውጋ ዘልቆ የሚያረሰርስ ቃል አለና ባፉ ሥሙን እየጠራሁ ልግባ ወደ እቅፉ ቃል ብቻ ይናገር እኔም እሰማለሁ ሸክሜን ሲያራግፈው ያኔ ሰው እሆናለሁ አዝ፦ የነፍሴ የውስጤ የልቤ የሚገባው ወዳጄ በቃሉ መጥቷል ወደ ደጄ ሲያንኳኳ ከፍቼ የክብርን ንጉሥ አስገባለሁ በአፉ ቃል ነፍሴን አጠግባለሁ