Song Lyrics

ንገሩልኝ መርዶ

ንገሩልኝ መርዶ ለዚያ ለጠላቴ(2x) ወጥመዱ ተሰብሮ ማምለጥ መፈታቴን (2x) ዳግም ላያገኘኝ ላልገባ በእጁ (2x) እግዚአብሔር አስቦኝ አዳነኝ በልጁ (2x) አመለጥኩት አመለጥኩት አመለጥኩት መሃላውን ቃልኪዳኑን አፈረስኩት አዲስ ኪዳን አደረግኩኝ ከኢየሱስ ጋራ በጐልጐታ ቀራንዮ በዚያ ተራራ (2x) የተተበተበው ሠንሰለት አስፈሪው የሕይወት ጨለማ በድንገት ጠፋ ገፈፍ አለ ከሰማይ አንድ ድምጽ ሰማ ሲተማመንብኝ ሲመካ ሲል አትወጣም ፍጹም ከእጆቼ የጌታዬ ፍቅር ማረከኝ ወጣሁኝ ሰይጣንን ከድቼ ከሕይወትም ሕይወት ከክብርም ክብር መውጣት ከጨለማ ከሙታን መንደር ለሰው በዘመኑ ይሄም አለ ለካ መስፈሪያ የሌው ሰላም ከቶ የማይለካ ንገሩልኝ መርዶ ለዚያ ለጠላቴ(2x) ወጥመዱ ተሰብሮ ማምለጥ መፈታቴን (2x) ዳግም ላያገኘኝ ላልገባ በእጁ (2x) እግዚአብሔር አስቦኝ አዳነኝ በልጁ (2x) አመለጥኩት አመለጥኩት አመለጥኩት መሃላውን ቃልኪዳኑን አፈረስኩት አዲስ ኪዳን አደረግኩኝ ከኢየሱስ ጋራ በጐልጐታ ቀራንዮ በዚያ ተራራ (2x) ከሰማያት የተላከውን የሕይወትን ጥሪ ደብዳቤ ከቶ እንዳልረዳ እንዳይገባኝ እንዳላስተውለው አንብቤ ባይኖቼ ላይ የተጋረደው የከበበኝ ያ የሞት ጥላ በቃሉ ጉልበት ተሰበረ በዙሪያዬ ብርሃን ሞላ መኖርስ ካልቀረ ትርጉም ያለው ኑሮ ለዘላለም ተድላ ከጌታ ጋር አብሮ አሁን ገና ደላኝ አሁን ተመቸኝ ከሁሉ የበለጠ ጌታ ኢየሱስ ያዘኝ ንገሩልኝ መርዶ ለዚያ ለጠላቴ(2x) ወጥመዱ ተሰብሮ ማምለጥ መፈታቴን (2x) ዳግም ላያገኘኝ ላልገባ በእጁ (2x) እግዚአብሔር አስቦኝ አዳነኝ በልጁ (2x) አመለጥኩት አመለጥኩት አመለጥኩት መሃላውን ቃልኪዳኑን አፈረስኩት አዲስ ኪዳን አደረግኩኝ ከኢየሱስ ጋራ በጐልጐታ ቀራንዮ በዚያ ተራራ (2x) የክብር አምላክ እግዚአብሔር ወደ ክብሩ አስጠግቶኛል ለዘለዓለም ማይናጋ ብርቱ ቅጥር ሰርቶልኛል ሺህ ቢፎክር ሺህ ቢዝትብኝ ጠላቴ ከየት ያገኘኛል የመስቀል ጀግና ጌታ ኢየሱስ ከመረቡ አስመልጦኛል ደሙ በጐበኔ ላይ ስለተቀባ የሞት መላእክተኛ ከቤቴ እንዳይገባ ይህ ለአምላኬ ደስታ መርዶ ለጠላቴ ሆኗል ለዘላለም (እሰይ) እኔ በማምለጤ ንገሩልኝ መርዶ ለዚያ ለጠላቴ(2x) ወጥመዱ ተሰብሮ ማምለጥ መፈታቴን (2x) ዳግም ላያገኘኝ ላልገባ በእጁ (2x) እግዚአብሔር አስቦኝ አዳነኝ በልጁ (2x) አመለጥኩት አመለጥኩት አመለጥኩት መሃላውን ቃልኪዳኑን አፈረስኩት አዲስ ኪዳን አደረግኩኝ ከኢየሱስ ጋራ በጐልጐታ ቀራንዮ በዚያ ተራራ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection