አዝ፦ ነግቶ እስከሚመሽ መሽቶም እስኪነጋ ስላንተ ብጫወት ስላንተ ባዎጋ እኔ አይሰለቸኝም አልታክትም ከቶ ምላሴም አይደክም ፍቅርህን አውግቶ አመሰግናለሁ ደግሜ ደግሜ እጅግ በገነነው ዙፋንህ ሥር ቆሜ በተመረጠ ቃል በሚጣፍጥ ዜማ የከንፈሬን ፍሬ መዝሙሬን ላሰማ ክበር እላለሁ (3x) ስትከብር እጠግባለሁ ንገሥ እላለሁ (3x) ስትነግሥ እረካለሁ እየደጋገሙ ሥሙን ለሚያነሱ የሚወዱትን ነው የሚያሞጋግሱ እኔም በአንተ ፍቅር ስለተያዝኩኝ ነግቶ እስከሚመሽ እጣራለሁኝ (2x) ጌታ እላለሁኝ አምላኬ እላለሁኝ ወዳጄ እላለሁኝ ረዳቴ እላለሁኝ አዝ፦ ነግቶ እስከሚመሽ መሽቶም እስኪነጋ ስላንተ ብጫወት ስላንተ ባዎጋ እኔ አይሰለቸኝም አልታክትም ከቶ ምላሴም አይደክም ፍቅርህን አውግቶ አመሰግናለሁ ደግሜ ደግሜ እጅግ በገነነው ዙፋንህ ሥር ቆሜ በተመረጠ ቃል በሚጣፍጥ ዜማ የከንፈሬን ፍሬ መዝሙሬን ላሰማ ክበር እላለሁ (3x) ስትከብር እጠግባለሁ ንገሥ እላለሁ (3x) ስትነግሥ እረካለሁ ሳይሰላቹና ፍፁም ሳይታክቱ ክብርን ይሰጡሃል በላይ መላዕክቱ እኔም ባለሁበት ድንኳን በጓዳዬ ለምወድህ ጌታ ይኸው ምሥጋናዬ (2x) ይብዛልህ ወብ አምልኮዬ ይብዛልህ ወብ ዝማርዬ ይብዛልህ ውብ ዕልልታዬ ይብዛልህ ውብ ምሥጋናዬ አዝ፦ ነግቶ እስከሚመሽ መሽቶም እስኪነጋ ስላንተ ብጫወት ስላንተ ባዎጋ እኔ አይሰለቸኝም አልታክትም ከቶ ምላሴም አይደክም ፍቅርህን አውግቶ አመሰግናለሁ ደግሜ ደግሜ እጅግ በገነነው ዙፋንህ ሥር ቆሜ በተመረጠ ቃል በሚጣፍጥ ዜማ የከንፈሬን ፍሬ መዝሙሬን ላሰማ ክበር እላለሁ (3x) ስትከብር እጠግባለሁ ንገሥ እላለሁ (3x) ስትነግሥ እረካለሁ ሥምህ በከንፈሬ ላይ እጅግ ጣፍጦኛል ባስታወስኩት ቁጥር ደስ ደስ ይለኛል አንዳንዴም ስደክም አቅም ሲከዳኝ አምላኬን ስጠራው እበረታለሁኝ (2x) ጉልበቴ እላለሁኝ ብርታቴ እላለሁኝ ድጋፌ እላለሁኝ ምርኩዜ እላለሁኝ አዝ፦ ነግቶ እስከሚመሽ መሽቶም እስኪነጋ ስላንተ ብጫወት ስላንተ ባዎጋ እኔ አይሰለቸኝም አልታክትም ከቶ ምላሴም አይደክም ፍቅርህን አውግቶ አመሰግናለሁ ደግሜ ደግሜ እጅግ በገነነው ዙፋንህ ሥር ቆሜ በተመረጠ ቃል በሚጣፍጥ ዜማ የከንፈሬን ፍሬ መዝሙሬን ላሰማ ክበር እላለሁ (3x) ስትከብር እጠግባለሁ ንገሥ እላለሁ (3x) ስትነግሥ እረካለሁ