ኦሆሆ አምላኬም ቢናገር ቢል እንደኔ ማን ነው እውነተኛነቱን እራሱን ቢያውቀው ነው የሚያመልኩት ሁሉ ቢሉ እንደ እርሱ ማን ነው መልካም አገዛዙን ፅድቁን ቀምሰውት ነው እኔ እላለሁ (3x) እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው እንደ አምላኬ ያለ ማን ነው ማን ነው (3x) አዝ፦ እንደ እግዚአብሔር/ጌታ ያለ ማንም የለምና በፅድቁ ተመካ/ልመካ በእውነቱ ተጽናና/ልጽናና እንደ ሰው አያይም አይበይንም እርሱ ፍርዱም ትክክል ነው ንፁህ ነው መቅደሱ (2x) ቁመተ ረዥም ሰፊ ትከሻ ለንጉሥነት አምላክ የሚሻ መሰለውና ተንጐራደደ እኔ ነኝ ብቁ ብሎ ፈረደ አምላኬ መቼ ሊያይ እንደ ሰው የፊት የፊቱን ከላይ ያለው እርሱ ወደ ውስጥ አጥርቶ ያያል ልበ ቀናውን መርጦ ይሾማል ቢረሳም እንኳን በሰዎች ከቶ በጌታ ፊት ግን ይታያል ጐልቶ ዳዊት ትንሹ ተጠርቶ መጣ ከታች ወደ ላይ በቅባት ወጣ ተንበሸበሽ በተስፋ ቃል ነገ በእስራኤል ንጉሥ ሊባል የተረሳውን የሚያይ አምላክ ለዘለዓለም ሥሙ ይባረክ አዝ፦ እንደ እግዚአብሔር/ጌታ ያለ ማንም የለምና በፅድቁ ተመካ/ልመካ በእውነቱ ተጽናና/ልጽናና እንደ ሰው አያይም አይበይንም እርሱ ፍርዱም ትክክል ነው ንፁህ ነው መቅደሱ (2x) ቢዶሉትብህ ቢመካከሩ በጥልቅ ጉድጓድ አንተን ሊቀብሩ ሞተሃል ብለው ቢነዙ ወሬ በዱር ሰጠመ ተበላ በአውሬ ሕልም አሳይቶ ተስፋ ሰጥቶሃል ለነፍሰ ገዳይ መች ይሰጥሃል በአሕዛብ ምድር ብትሰደድም የያዝከው ተስፋ መሆኑ አይቀርም በግብጽ ምድር ብትሆን ግዞት የተነገረህ ቃሉ እርሱ አይሞት ጊዜን ጠብቆ ይከናወናል አሳዳጆችህ ይሰግዱልሃል ቢመስልም ነገር የተጓተተ የሌላው ሚስጥር ሲፈታ በአንተ በተጣልክበት አብሮ የሆነው የእስራኤል አምላክ እርሱ እግዚአብሔር ነው አዝ፦ እንደ እግዚአብሔር/ጌታ ያለ ማንም የለምና በፅድቁ ተመካ/ልመካ በእውነቱ ተጽናና/ልጽናና እንደ ሰው አያይም አይበይንም እርሱ ፍርዱም ትክክል ነው ንፁህ ነው መቅደሱ (2x) ሀማ ቢፎክር ቢያኖር መስቀያ አንተ ግን ዘምር በኃሌሉያ ሲያልፍ ሲያገድም ቁጭ በል በፊቱ የእጁን ልትቀማው ደርሷል ሰዓቱ ንጉሡ ስለ አንተ ይቀሰቀሳል መዝገብን ይዞ ያገላብጣል ያን ጊዜ ነገር ይለዋወጣል ሹሙት አንግሡ ቀቡት ይባላል አምላክህ ፃዲቅ ፈራጂ ነውና ሳትደናገጥ ጠብቅ ቁምና በፊትህ መውደቅ የጀመረው ፈጽሞ ይወድቃል ድል የአንተ ነው በአንተ ጀምሮ በአንተ ይፈጽማል የአይሁድ መዳን ይረጋገጣል መርደኪዮስ ሆይ አባክህ ፅና የጌታን ክብር ልታይ ነውና አዝ፦ እንደ እግዚአብሔር/ጌታ ያለ ማንም የለምና በፅድቁ ተመካ/ልመካ በእውነቱ ተጽናና/ልጽናና እንደ ሰው አያይም አይበይንም እርሱ ፍርዱም ትክክል ነው ንፁህ ነው መቅደሱ (2x)