Song Lyrics

ሙሽራዪቱ ሆይ ተነሺ

Azeb Hailu
Ashenafi Negn
የልዑሉ አምላክ ማደሪያ አካሉ የሆንሽ የእርሱ መኖሪያ አንች ቤተክርስቲን ተነሺ የሰጠሽን ተስፋ አትርሺ ሁኝ እንጂ ልክ እንደ ሙሽራ ልትቆሚ እኮ ነው በተራራ የሰርግሽ ቀን በጣም ቅርብ ነው ሙሽራሽ ደጂ እያንኳኳ ነው ዘምሪለት እንጂ በዕልልታ የምን በራድ ትኩስ ለብታ ድመቂ ንሺ ተቀደሽ ሙሽራይቱ ሆይ ተነሽ መቅረዝሽ በዘይት ይሞላ በር እንዳይዘጋብሽ ኋላ ቀን ሳላ ዛሬ ተዘጋጂ በፍጻሜው እንዳትጐጂ ረሻሽ ወይ ጌታሽ መመለሱን ጠብቂኝ እመጣለህ ማለቱን መዘናጋቱ ምነው በዛ ጣል እረግሽው ልክ እንደዋዛ የወደፊቱ ክብር ተስፋ ተጋረደ ከዓይንሽ ስር ጠፋ ጊዜው ደርሷል እባክሽን ንቂ ቤተክርስቲያን ተጠንቀቂ ሊያደርግሽ ፍሬ አልባ ገለባ የዓለም ኮተት ሰርጐ ገባ ተኝተሽ ጠላት ዘሩን ዘራ ምድርሽ እንክርዳድን አፈራ በበጉ ደም ፈጥነሽ ታጠቢ አስታውሺ ተስፋሽን አስቢ የሰርጉ ቀን በጣም ተቃርቧል ሙሽራሽ ወደ አንቺ ይመጣል አሜን ማራናታ ቶሎ ና የምትይበት ጊዜው ነውና ይሰማ ድምፅሽ ያስተጋባ ወደ ልዑል ማደሪያ ይግባ ከእንግዲህ በምድር ምን ቀረሺ ናፍቂ ወደሰማይ ገስግሺ ይልቃል በዚያ ያለው ደስታ ማሰማት ዝማሬና ዕልልታ በዚያ እኮ ርሃብ ጥማት የለም ደዌ ህመም አይታወቅም እንባ ከዓይኖችሽ ይታበሳል በጉ የአንች እረኛ ይሆናል የበጉ መሽራ አንቺ ሆይ ይህ ክበር አልናፈቀሽም ወይ ይመጣል ወዳጅሽ ወደ አንቺ ተነሽ ቁሚ ተዘጋጂ ማራናታ ማራናታ አሜን ጌታ ሆይ ተሎ ና አሜን ኢየሱስ ተሎ ና አሜን ጌታ ሆይ ተሎ ና አሜን ኢየሱስ ተሎ ና (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection