Song Lyrics

እያስገረመኝ

Azeb Hailu
Ashenafi Negn
ውለታውን ተናግሮ ያበቃ እግዚአብሔርን አክብሮ የረካ ማነው እርሱ ምሥጋና ያለቀበት ያልተረዳ የዛሬውን ምህረት ከትናንቱ በላይ እንደሆነ በብዙ . (1) . እንደገነነ የዛሬውን ቸርነት/ደግነት የረሳ ለማመሥገን በፍጥነት ይነሳ (2x) አዝ፦ እኔስ ከትናንቱ የዛሬው ባሰበኝ ካለፉት ዓመታት የሆነው ላቀብኝ ፍቅር ደግነቱ ምህረቱ ገነነ ከማስበው በላይ መልካም የሆነ እያስደነቀኝ ሁሌ እያሳቀኝ አፌን በምስጋና ምላሴን በዕልልታ እየሞላብኝ ነፍሴን የሚያረካ ክብሩን እያሳየኝ እንዴት ዝም እላለሁ ዘወትር በየለቱ ሁልጊዜ ጌታዬ አመሠግናለሁ (5x) ተናግሬ ሳልጨርስ ተዓምሩን ይገልጠዋል ክብሩን በላይ በላይ እየጨማመረ እያበዛ ደግሞ እያከበረ በዘመናትና በዓመታቱ ሳያጓድል ሳይሰስት ንብረቱን ያስጉዘኛል/ያስኬደኛል በድል ሰረገላ ምን ልበለው ከተመሥገነ ሌላ (2x) አዝ፦ እኔስ ከትናንቱ የዛሬው ባሰበኝ ካለፉት ዓመታት የሆነው ላቀብኝ ፍቅር ደግነቱ ምህረቱ ገነነ ከማስበው በላይ መልካም የሆነ እያስገረመኝ እያስደነቀኝ ሁሌ እያሳቀኝ አፌን ምላሴን በዕልልታ እየሞላብኝ ነፍሴን የሚያረካ ክብሩን እያሳየኝ እንዴት ዝም እላለሁ ዘወትር በየለቱ ሁልጊዜ ጌታዬ አመሠግናለሁ (5x) ማዳኑን ስላየሁ አመሠግናለሁ (3x) ፍቅሩን ቀምሼ እንዴት ዝም እላለሁ (3x) ቀኖቹ ቢያወሩ ቢመሰክሩት (3x) አቤት ለእኔ ያደረገው ድንቅ ተዓምራት (3x) ሥሙን እባርከዋለሁ (3x) ሥሙን እቀድሰዋለሁ (3x) ነፍሴና ሥጋዬ ምሥጋና ለእግዚአብሔር አቅርቡ አጥንቶቼም ጭምር ምሥጋና ለእግዚአብሔር አቅርቡ የሰራላችሁን የማዳኑ ሥራ አስቡ (2x) አልበቃኝም አመሥግኜው (2x) አልበቃኝም እኔ አልረካሁም አመሥግኜው (2x) አልረካሁም (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection