Song Lyrics

ካህኔ

Azeb Hailu
Ashenafi Negn
በሞት ያልተሻረ በሞት ያልተገታ በሰማይም ቀጥሏል ክህነቱ የጌታ ሌሎቹ እንዳይኖሩ ሞት ከልክሏቸዋል ከነአሮን ክህነት የኢየሱስ ይበልጣል ካህኔ እንደመልከጼዴቅ ካህኔ ለዘላለም ሹም ነህ ካህኔ ለኔም ሕይወት መዳን ካህኔ ምክንያቱ አንተ ነህ ካህኔ በማይጠፋው ክህነት ካህኔ በማይሽረው ሞት ካህኔ የምትማልድልኝ ካህኔ ቆመህ በአብ ፊት ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ ምን እሰጣለሁ ከማመስገን በቀር በማለዳ በቀትር በማታ አምላኬ ሆይ ልበል ክበር ክበር (2x) ካህኔ በአብ ቀኝ ያለሀው ካህኔ የነፍሴ ጠበቃ ካህኔ መከራዬ እንዲቆም ካህኔ ሀዘኔ እንዲያበቃ ካህኔ የጥልን ግድግዳ ካህኔ በሞት አፈረስህ ካህኔ ለበደሌ መስዋዕት ካህኔ ደምህን አፈሰስህ በሞት ያልተሻረ በሞት ያልተገታ በሰማይም ቀጥሏል ክህነቱ የጌታ ሌሎቹ እንዳይኖሩ ሞት ከልክሏቸዋል ከነአሮን ክህነት የኢየሱስ ይበልጣል የካህናት አለቃ የበጎች እረኛ የእውነተኛዋ ድንኳን መካከለኛ በኔ ፈንታ የሞተ የሆነልኝ በዛ ነፍሴ በጣም ረክታለች ለእርሱ ስትገዛ መድህኔ የመቀበርያዬን መድህኔ ጉድጓድ የደፈንከው መድህኔ የሕይወቴን ጨለማ መድህኔ ገለል ያደረከው መድህኔ በሞትና በኔ መድህኔ መካከል ገብተህ መድህኔ ሕያው አደረከኝ መድህኔ አንተ ተችሎህ ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ ምን እሰጣለሁ ከማመስገን በቀር በማለዳ በቀትር በማታ አምላኬ ሆይ ልበል ክበር ክበር (2x) መድህኔ ዛሬስ ብርሃን ነው መድህኔ ቀን ሆኖ ለነፍሴ መድህኔ ባንተ ተሰበረ መድህኔ ለቅሶና ትካዜ መድህኔ ፍጻሜዬ እንዲያምር መድህኔ የመጨረሻዬ መድህኔ አንተን መጠጋቴ መድህኔ ልክ ነው ምርጫዬ ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ ምን እሰጣለሁ ከማመስገን በቀር በማለዳ በቀትር በማታ አምላኬ ሆይ ልበል ክበር ክበር (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection