Song Lyrics

ሥሙ ሞገሳም ነው

Azeb Hailu
Ashenafi Negn
ወዶ አይደለም ፍጥረት ሰዎች የሚርበደበደው ከወዲህ ተጠርቶ ከማዶ ይሰራል ድንገት ደርሶ የጠላትን ምሽግ ያሸብራል አዝ፦ ኢየሱስ የሚለው ሥም ብርቱ ጉልበት አለበት አይቻለሁ ጠላቶቼ ሲመታ ሲያንቀጠቅጥ (2x) እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያረገው ከሥም ሁሉ በላይ ሥምም የተሰጠው በሰማይም ኢየሱስ ነው በምድርም ኢየሱስ ነው ከምድር በታች ኢየሱስ ነው በሁሉ ላይ ኢየሱስ ነው (2x) የበሽታ ብርታት የደዌ ጉልበት አይፈልግም የጌታ ሥም እንዲጠራበት በሥጋ ለባሽ ላይ የሚበረታው ያውቃል ከተጠራ ሥሙ እንደሚነቅለው አዝ፦ ኢየሱስ የሚለው ሥም ታላቅ ጉልበት አለበት አይቻለሁ ለህመሜ ሲሆን መድኃኒት (2x) እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያረገው ከሥም ሁሉ በላይ ሥምም የተሰጠው በሰማይም ኢየሱስ ነው በምድርም ኢየሱስ ነው ከምድር በታች ኢየሱስ ነው በሁሉ ላይ ኢየሱስ ነው (2x) የመከራን ጭጋግ የሚችል መግፈፍ በእውነተኛው በረከት የሚያትረፈርፍ የባዶ ሸለቆ የመሙላት ሚስጥር ሲጠራ ነው የኢየሱስ ሥም በታላቅ ክብር አዝ፦ ኢየሱስ የሚለው ሥም ደግነትም አለበት አይቻለሁ በጓዳዬ ሲሆንልኝ በረከት (2x) እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያረገው ከሥም ሁሉ በላይ ሥምም የተሰጠው በሰማይም ኢየሱስ ነው በምድርም ኢየሱስ ነው ከምድር በታች ኢየሱስ ነው በሁሉ ላይ ኢየሱስ ነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection