Song Lyrics

ሚስጥርን የሚገልጽ

Azeb Hailu
Ashenafi Negn
ሚስጥርን የሚገልጥ በሰማይ ውስጥ አለ ዙፋኑ በብዙ ክብር የተከለለ ከሰው ልብ የጠፋን ህልም ከነፍቺው የሚያቀብል አምላክ እግዚአብሔር ነው (2x) ዙፋኑ በሰማይ ርቆ ከፍ ቢልም በዓይኖቹ ከማየት ፍፁም አይታክትም የተሰወረውን በታች በሸለቆ እርሱ ወደ ብርሃን ይገልጠዋል አውቆ (2x) አዝ፦ ማነው ከፊቱ የሚሰወር ማነው ከእርሱ የሚደበቅ ማነው ወጥቶ የሚገባ ማነው አምላኬ ሳያውቅ ያያል ያያል ሁሉን ነገር ያያል ያውቃል ያውቃል አስተውሎ ያውቃል ዝም ቢል ቢታገስ ለፍርድ ባይቸኩል የተወህ የረሳህ ያላየህ አይምሰልህ (2x) የቀድሞውን ዘመን ወይንም የአሁኑ ገና የሚመጣውን የወደፊቱን የፍጥረትን ሩጫ ሙሉ እንቅስቃሴ እርሱ ብቻ ያውቃል አምላኬ ንጉሤ (2x) ነገር ሁሉ ፊቱ ዕርቃኑን ይቆማል ማን ከእርሱ ሚስጥሩን ደብቆ ያኖራል የሰማይ የምድሩን ሁሉንም አዋቂ ከስውርም ወጥመድ አዳኝ ነው ነጣቂ (2x) አዝ፦ ማነው ከፊቱ የሚሰወር ማነው ከእርሱ የሚደበቅ ማነው ወጥቶ የሚገባ ማነው አምላኬ ሳያውቅ ያያል ያያል ሁሉን ነገር ያያል ያውቃል ያውቃል አስተውሎ ያውቃል ዝም ቢል ቢታገስ ለፍርድ ባይቸኩል የተወህ የረሳህ ያላየህ አይምሰልህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection