Song Lyrics

የሕይወቴ መመሪያ

Azeb Hailu
Ashenafi Negn
አዝ፦ ማለዳ አግኝቼው ቀን ይናፍቀኛል ቀትር ላይ አይቼው ምሽት ይርበኛል የሕይወቴ መመሪያ ፅኑ መሠረቴ ትለዋለች ነፍሴ ቃልህ ቁርስ እራቴ (2x) ባናበብኩት ቁጥር ባሰላሰልኩት በዝቶ ይበራልኛል የቃልህ እውነት ያኔ ደግሞ ነፍሴ ትረሰርሳለች የምድሩን ረስታ ወደላይ ታያለች አሁንም አሁንም ስትሻህ ደጋግሞ ልክ እንደ ዋላዋ ቃልህን ስትጠማ ቢገባት ነው ነፍሴ የጋለ ውበቱ ጠንካራውን ልቤን ማሸነፍ መርታቱ ተማርኪያለሁ በቃልህ ውበት ተስቢያለሁ ተማርኪያለሁ ሕይወቴን ለእርሱ ሰጥቻለሁ ተማርኪያለሁ በቃልህ ፍቅር ተይዣለሁ ተማርኪያለሁ ቶሎ ቶሎ ፈልገዋለሁ እየኮረኮረ ገብቶ ወደ ሕይወቴ ለውጦ አስቀረው የውስጥ ማንነቴን ልቤም ተሸነፈ ተረታ በቃልህ አምሮ ተሸላልሞ ማደሪያህ ሆነልህ እንዳንበረከከው ግዛው ሠልጥንበት በሁለንተናዬ አንተው ንገሥበት ይንኮርኮር በልቤ ምክር ተግሳፅህ ሲነጋም ሲመሽም ምን ጊዜም ልስማህ አዝ፦ ማለዳ አግኝቼው ቀን ይናፍቀኛል ቀትር ላይ አይቼው ምሽት ይርበኛል የሕይወቴ መመሪያ ፅኑ መሠረቴ ትለዋለች ነፍሴ ቃልህ ቁርስ እራቴ (2x) መንፈሴም ታደሰ ውስጤ በረታታ ሲለቀቅ ወደ እኔ ቃልህ ጠዋት ማታ ከዓይኔ ላይ ተነሳ ቅርፊቱም ወደቀ የሕይወቴም ብርሃን በቃልህ ደመቀ ዛሬም አዲስ ነገም ሁሌም ነው አዲስ ሲገለጥ እውነትህ ለልብ ለመንፈስ እውነትም የሕይወት ቃል ነህ መድኃኒቴ አረፈች ከአንተ ጋር ተጣብቃ ሕይወቴ ተማርኪያለሁ በቃልህ ውበት ተስቢያለሁ ተማርኪያለሁ ሕይወቴን ለእርሱ ሰጥቻለሁ ተማርኪያለሁ በቃልህ ፍቅር ተይዣለሁ ተማርኪያለሁ ቶሎ ቶሎ ፈልገዋለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection