Song Lyrics

ሽሽ እንጂ

Azeb Hailu
Ashenafi Negn
እያሳሳቀ ይወስዳል ውኃ ወደ ሙት አገር ወደ በረሃ እዳር ዳር ማለት በኃጥያት ሰፈር ወድቆ ለማንባት ለመሰባበር ሽሽ እንጂ ማነው ያለህ ተጠጋ በጠላትህ ቀስት እንዳትወጋ ኃጢአት አይምርም አንተን አግኝቶ የሚሻለው ግን ማምለጥ ነው ሸሽቶ ይቅርብህ እንዲያው በዋል ፈሰስ ይቅርብህ በሕይወት/በነፍስ ላይ አመፅ ይቅርብህ እንዲያው ወጣ ገባ ዕድሜህን አታድርገው የእንባ (2x) ቅጥርን የሚያፈርስ እንደሚነደፍ ከፅድቅ ክሌ አትውጣ አትለፍ እንደ ተራበ ሆኖ እንደ አንበሳ ይጠብቅሃል ክፉ እያገሳ ፈቀቅ ብትል አንዲት እርምጃ መመለስህን መምጣትህን እንጃ የተከፈተው የአውሬው መንጋጋ ውጦ ያስቀርሃል አትዘናጋ መለስ እስኪ አንዴ በል መለስ አስብ በእርጋታ አይሻልም ዎይ መኖር በጌታ የሚያስጐመጀው ሁሉ አይበላ ሞትን ደብቆ ይዟል ከኋላ አትንካ ካለህ ቅዱስ አምላክህ ስለሚያውቅ ነው አስተውል ባክህ እሳትን እሳት አቅፎ በጉያው በአንዲት ሌሊት ነዶ ይጋያል ኃጢአት አድብቶ ቆሟል በደጅህ እባክህ አትተኛ ነቃ በል እንጂ ይቅርብህ እንዲያው በዋል ፈሰስ ይቅርብህ በሕይወት/በነፍስ ላይ አመፅ ይቅርብህ እንዲያው ወጣ ገባ ዕድሜህን አታድርገው የእንባ (2x) ይቅርብህ (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection