ሙሉ መስዋዕት እንከን የሌለው ኦሆ ለአማልክት አምላክ ይዣለው ኢኸው አሃ የማያነክስ ወይ ያልታወረ ኦሆ ለጌቶች ጌታ ለተከበረ አሃ በፊቱ የተወደደ በፊቱ ከቶ ያልተናቀ ሊያሸተው በአምላኬ ዘንድ ዘወትር የተናፈቀ ቅዱሱም ሕያው መስዋዕት እራሴ ነው ሰውነቴ ላፍስሰውና ልሰዋው ደስ ይበለው መድኃኒቴ አዝ፦ ለአምላኬ ምሥጋናዬን እሰዋለሁ ለንጉሡ ስዕለቴን እከፍላለሁ ይህ ለእኔ ሥራዬ ነው ልማዴ በወቅቱ ክብርን መስጠት ለውዴ ይሄ ነው ልማዴ (3x) ሙሉ ለሙም ጭሶ የሚቃጠል ኦሆ በዙፋኑ ላይ እሰይ የሚያስብል አሃ ያለቁጠባ ያለ ስስት ኦሆ በማደሪያው ላይ ይሽተትለት አሃ ከነፍሴ ከፍፁም ደስታ የነፍሴ ነው ከፍቃዴ በጠዋትና በማታ የምሰዋለት ለውዴ የተመረጠውን መስዋዕት ከስቡና ከበኩሩ አምላኬን ደስ ካሰኘው ይኸው ለዝናው ለክብሩ አዝ፦ ለጌታ ምሥጋናዬን እሰዋለሁ ለልዑሉ ስዕለቴን እከፍላለሁ ይህ ለእኔ ሥራዬ ነው ልማዴ በወቅቱ ክብርን መስጠት ለውዴ ይሄ ነው ልማዴ (3x) የደመናትን ድንበር የሚጥስ ኦሆ ወደ ማደሪያው የሚገሰግስ አሃ የተወደደው ውድ ምሥጋና ኦሆ የተገባው አምላክ ነውና አሃ በምድር እስካለሁባት እስከ ኖርኩባት ዘመኔ የሚገባውን በሙሉ አላጓድልም ከእኔ በማንኛውም ሁኔታ በማንኛውም ሰዓት እርሱ ይቀበለኝ እንጂ አልሰለችም መሰዋት አዝ፦ ለአምላኬ ምሥጋናዬን እሰዋለሁ ለንጉሡ ስዕለቴን እከፍላለሁ ይህ ለእኔ ሥራዬ ነው ልማዴ በወቅቱ ክብርን መስጠት ለውዴ ይሄ ነው ልማዴ (5x)